Get Mystery Box with random crypto!

ኢማንን የሚጨምሩ ነገሮች ኢማንን የሚጨምሩ ነገሮች በርካታ ሲሆኑ ከነዚህ | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

ኢማንን የሚጨምሩ ነገሮች

ኢማንን የሚጨምሩ ነገሮች በርካታ ሲሆኑ ከነዚህ መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ፡-
ጠቃሚ የሆነ እውቀት መማር፤ የተከበረውን ቁርኣን በማስተንተን መቅራት፤ የአላህን መልካም ስሞችና ከፍተኛ የሆነውን መገለጫ ማወቅ፤ የኢስላምን ሓይማኖት ውበትና መልካምነት መገንዘብ፤ የነብያችን ﷺ እና የተከበሩትን ሶሃቦች ታሪክ
መማር፤ በዚህ ሰፊ የሆነ አለም ውስጥ ያለውን የአላህ ተዓምር ማስተንተን ናቸው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡-

رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ
«ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡አል ኢምራን፡ 191

የአላህን ትእዛዝ አጥብቆ መያዝ፤ ወደአላህ መቃረብን አላማ በማድረግ ዒባዳዎችን በጥንክርና ተፈጻሚ ማድረግ ኢማንን ይጨምራል፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡-

‟وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَمَعَ الْمُحْسِنِينَ

‟እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡
አንከቡት፡ 69

ኢማንን የሚያጓድሉና የሚቀንሱ ነገሮች፡-
በአላህ ዲን ላይ ማህይም (ጃሂል) መሆን፤ አኼራን መርሳት ወይም መዘንጋት፤ ከአላህ ህግ ማፈንገጥ፤ ወንጀል መስራት፤ በመጥፎ ለምትጎተጉት ነፍስ ታዛዥ መሆን፤ ከአመጸኞች ጋር መቀላቀል፤ ስሜትን እና ሰይጣንን መከተል፤ በዱንያ መሸንገል፤ ዱንያን የመጨረሻ ትልቁ ዓላማና ግብ ማድረግ ናቸው፡፡

‟روى الحاكم في"المستدرك"من حديث عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال":إن الإيمان ليخلق في جوف أحدكم كما يخلق الثوب الخلق ، فاسألوا الله أن يجدد اإليمان في قلوبكم"
‟ የአላህ መልክተኛ ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“ልክ ልብስ እንደሚያልቀው ኢማን በአንዳችሁ ውስጥ ያልቃል ፤ በልቦቻችሁ ውስጥ ኢማንን እንዲያድስላችሁ አላህን ለምኑት፡፡”
ሃኪም ፊልሙስተድረክ፡ 5
ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂሁ አልጃሚዕ፡ 1590

ኢማንን ለማደስ ነብዩ ﷺ የሚከተለውን አቅጣጫ ሰጠዋል፡-
"فاسألوا الله أن يجدد اإليمان في قلوبكم"
“ኢማንን በልቦቻችሁ ውስጥ እንዲያድስ አላህን ጠይቁ፡፡

ኢማናችንን እንዲያድስልን፣ እንዲያጠነክርልንና እንዲያመቻችልን አላህን ችክ ብሎ መለመን ያስፈልጋል፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡-

يُثَبِّتُ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا بِالْقَوْلِ الثَّابِتِ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ

‟አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል፡፡
ኢብራሒም፡ 27

ኢማንን በልቦና ውስጥ ለማረጋገጥ ወይም ለማሟላት እያንዳንዱ ሰው የራሱን ጥረት ማድረግና መታገል አለበት፡፡ የዚህ ማህበረሰብ ቀደምቶች ለዚህ ትልቅ አብነት ናቸው፡፡ ኢማንን ወደራሳቸው ለማምጣት ከፍተኛ ትግል አደረጉ፤ ኢማን ከምግብ፣ ከመጠጥ እና ከአየር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ተገነዘቡ፡፡ እምነታቸውን በየጊዜው አደሱ፤ ኢማን የሚጨምሩ ነገሮችን ሰሩ፤ በዚህም ትክክለኛ የሆነውን ኢማን አረጋገጡ፡፡

ዑመር  ለጓደኞቹ “ኑ ወደዚህ እምነታችንን እንጨምር” ይላቸው ነበር፡፡

ዓብደላህ ብን መስዑድ ደግሞ  “ኑ ከእኛ ጋር ተቀመጡ ኢማናችንን እናድስ” ይል ነበር፡፡ የሚከተለውን ዱዓም ያደርግ ነበር ፡- “አላህ ሆይ! ኢማንን ጨምርልን፤ እርግጠኝነትን ስጠን”
ዓብደላህ ብን አህመድ ፊ አስሱንና፡ 797

ዓብደላህ ብን ረዋሃ 4 የጓደኞቹን እጅ ይዞ “እርሱን በመታዘዝ በምህረቱ እንዲያስታውሰን ኑ! የተወሰነ ሰዓት እንመን፤ አላህን እናስታውስ፤ ኢማናችንን እንጨምር” ይል ነበር፡፡
ኢብኑ አቢ ሸይባህ፡ 30426

አቡደርዳእ ደግሞ “እምነታቸው ከሚጨምርላቸው ሰዎች ነኝ? ወይስ ከሚጎድልባቸው? የሚል ጥያቄ ለነፍሱ የሚጠይቅ ከሆነ ይህ ሰው የእውቀት ባለቤት ለመሆኑ አመላካች ነው” ይል ነበር፡፡ ይህ ማለት አንድ ሰው ሰይጣን በየት በኩል መጦ እንደሚጎተጉተው ካወቀ ይህ ሰው የእውቀት ባለቤት ለመሆኑ አመላካች ነው ማለት ነው፡፡ አልኸላል ፊ አስሱናህ፡ 1585
ኢብኑ በጣህ ፊ አልኢባነቲ አልኩብራ፡ 1140

ዑመይር ብን ሀቢብ  የሚከለተለውን ይናገር ነበር “ኢማን ይጨምራል ይቀንሳል”፤ “ምንድን ነው መጨመር መቀነስ” የሚል ጥያቄ ቀረበለት፤ “አላህን ስናስታውስ፤ ስናመሰግነው፤ ስናጠራው ይህ ነው የኢማን መጨመሩ፤ ስንዘነጋ፤ (ፈርዶችን) ስንተው ስንረሳ ደግሞ ይህ ነው የኢማን መጉደል” የሚል ምላሽ ሰጠ፡፡
ኢብኑ አቢ ሸይባህ
ዓብደላህ ብን አህመድ ፊ አስሱንናህ ፡ 624

"የኢማን ትሩፋት ኢማን ይጨምራል ይቀንሳል" ከሚለው ሪሳላህ የተወሰዴ!!

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
   ሼር JoiN & Share
http://t.me//@arebgendamesjid
    ።።።።።።።።።።።። ።።።።።።።።።

شباب عرب غندي مسجد