Get Mystery Box with random crypto!

የነፍስ መከናወን (Soul Making)! የነገረ መለኮት ሊቁ ጆን ሂክ (John Hick) “Phi | ናዝራዊ Tube

የነፍስ መከናወን (Soul Making)!

የነገረ መለኮት ሊቁ ጆን ሂክ (John Hick) “Philosophy of Religion” የሚል ግሩም መጽሐፍ አላቸው፡፡ በዚህ መጽሐፋቸው (ገጹን ዘነጋሁ) እንዲህ ይላሉ፡-This world has the potential of pain and evil but it also provides the opportunity for growth and character development!

ታዲያ ይህንን የምናልፍበትን ሂደት “Soul Making” ብለው ነው የሚጠሩት፡፡ ይህንን ስያሜ ሐዋርያው ዮሐንስ በመልእክቱ እንዳሰፈረው የነፍስ መከናወን እንበለው ይሆን? “ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ።” (3ዮሐ.1፥2) ብሏልና!

ሐዋርያው “ነፍስህ እንደሚከናወን/ as your soul prospers” ሲል፣ እኛ አማኞች በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ስናልፍ የሚመጣውን መንፈሳዊ ብስለት መናገሩ ነው ብዬ ነው የወሰድኩት፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ በሂደቱ ሐዋርያው ያዕቆብ የሚመጣውን መከናወን “ፍጹማንና ምሉዓን/ mature and complete” መሆናችን እንደ ሆነ መውሰድ እንችላለን ብዬ አስባለሁ።

“ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤ ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።….Let perseverance finish its work so that you may be mature and complete, not lacking anything.” (ያዕ.1፥2-4)፡፡

ታዲያ Soul Making (የነፍስ መከናወን) ትርፉ ታላቅ ከሆነ ከእኛ የሚጠበቀው ምንድነው? በጥበቡ ከፍ ያለው ጌታ እንደ ወደደ እንዲሠራን “እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” ብሎ መታመን ነዋ!

ጌታ ሆይ፣ የምናልፍባቸው ሂደቶች የሚያሳምሙ ቢሆኑም፣ ነፍሳችን በአንተ ላይ እንድትደገፍ ጸጋህን አብዛልን!

Dr. Beke
@nazrawi_tube