Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ የጆን ካልቪን የልደት ቀን ነው። ( July 10, 1509 - May 27, 1564)። ልደቱን | ናዝራዊ Tube

ዛሬ የጆን ካልቪን የልደት ቀን ነው። ( July 10, 1509 - May 27, 1564)። ልደቱን ስናስብ ቀጥሎ ያሉትን ሁለት ማሳሰቢያዎች ልተውላችሁ:-

ከሐዋርያው ከጳውሎስ:-

“ከሙታን የተነሣውን፣ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤ የእኔም ወንጌል ይኸው ነው።” (2 ጢሞ. 2:8)

ከካልቪን:-

“እረኞች በቃሉ እውነት ደፋሮች ይሁኑ . . . ማንኛውንም የዓለም ኅይል፣ ክብርና ልቀት ለቃሉ መለኮታዊና ግርማዊነት ያስገዙ። ከትልቁ እስከ ትንሹ ሁሉን በቃሉ ሥልጣን ይምሩ፤ የክርስቶስንም አካል ያንጹ። የሰይጣንን አገዛዝ ያፍርሱ፤ መንጋውን ያሰማሩ፤ ተኩላውን ይግደሉ፤ ዐመፀኛውን ይገስጹ፣ ይምከሩም። ካስፈለገም ነጐድጓድና መብረቁን ይሰሩና ይፍቱ፤ ነግር ግን ሁሉን እንደ እግዚአብሔር ቃል ያድርጉ። ” (Sermons on the Epistle to the Ephesians, xii).

ጌታችን ሆይ፣ “ክብርህን ተጠሚዎች፣ ቅዱስ ቃልህን ብቻ ሰባኪዎች፣ ለራሳቸው ፈቃድ የሞቱ ታማኝ ባሪያዎችና የወንጌል ዐደራ ጠባቂዎች አድርገን።”

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)
@nazrawi_tube