Get Mystery Box with random crypto!

የቱንም ያህል ብንወራጭ መቼ እንደሆነ ነው የማናውቀው እንጂ የሆነ ቀን የሆነ ቦታ በሥጋ እንደ ተወ | ናዝራዊ Tube

የቱንም ያህል ብንወራጭ መቼ እንደሆነ ነው የማናውቀው እንጂ የሆነ ቀን የሆነ ቦታ በሥጋ እንደ ተወለድናት ከሥጋ እንለያታለን፡ ቤንጃሚን ፍራንክሊን ተናገሩት እንደሚባለው ከሆነ በዚህ ዓለም ውስጥ ከሞትና ከግብር በስተቀር ምንም ነገር እርግጠኛ አይደለም፡ የግብሩን እርግጠኞች ባንሆንም ከቀን ወደ ቀን ሞት በሰውነታችን እየጨመረ ስለሚሄድ የሥጋን ሞት ልንክደው አንችልም።

በዚህ ዓለም ውስጥ በመወለድ “እልልልል….” በመሞት ደግሞ “ወዮ…” ማለት ብርቅ አይደለም፡ ነገር ግን ትልቁ ጉዳይ መወለድና መሞቱ ሳይሆን በመወለድና በመሞት መካከል የምንሆነው ነገር ወይም የምንኖረው ኑሮ ነው።

እነዚህ ከታች ምስላቸው የሚታየው ሰዎች ይብዛም ይነስም እንደ ተቀበሉት ፀጋና እንደ አቅማቸው፣ እንዲሁም በገባቸው መጠን የወንጌልን ስራ ወይም የእግዚአብሔርን ሐሳብ አገልግለው ባለፉት 15 ዓመታቶች ውስጥ በሥጋ ከተለዩን ወገኖች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

መጽሃፍ የሚለውን የምናምን ከሆነ እያንዳንዳችን በሥጋ ለሰራነው ብድራት እንቀበል ዘንድ በክርስቶስ ፊት እንቀርባለን፡ ሰው እንደ ጳውሎስ፣ ወይም እንደ ጴጥሮስ፣ ወይም እንደ አጵሎስ ሊሮጥ ይችላል፤ መጨራሻ ላይ ግን ሁሉ ብድራቱን ያገኛል፡ ብድራቱ ታዲያ እዚህ ሰዎች በሰፈሩን ልክ ወይም በሚሰፍሩበት መስፈሪያ ሳይሆን ጻድቅ ፈራጅ በሚሰፍርበት መስፈሪያ ነው፡ በሥጋ ለተለዩን ብናዝንም ለራሳችን “ማዘንን” ግን አንርሳ፤ ገና ሮጠን አልጨርስንምና፡ ዛሬ ወይም ነገ ልንጠራ እንችላለን: እስተዛ ግን እድል አለን: ምን ይታወቃል፣ ነገ ሲነጋ ፌስ ቡክ ላይ አልፅፍ ይሆናል::

ጉዳዩ የሥጋ ቆይታችን ማጠሩና መርዘሙ ሣይሆን በአጭሩም ቢሆን በረዥሙ ከእሣት የሚያልፍ ስንቅ ይዞ መሄዱ ላይ ነው፡ እዚያ ያለው ቋታችን የሚሞላው እዚህ በጣልነው ልክ ነው::

ማርቲን ሉተር እንዲህ ይሉ ነበር:-

"ካላንደሬ ላይ ሁለት ቀኖች ብቻ ናቸው ያሉት - this day and that day”

እውነታቸውን ነው!
ነገር ግን that dayአችን በ this dayአችን ይወሰናል::

ትሞታለህ ትሞቻለሽ እሞታለሁ እንሞታለን

ዕብራውያን 12 ፡ 1 - 2

እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።

ከyilu danu fb የተወሰደ
@nazrawi_tube