Get Mystery Box with random crypto!

ቁልፉን ትቶ ዳቦውን?! _____________ በምስሉ የምንመለከተው ሰው በታሰረበት ክፍል ሆኖ በፊ | ናዝራዊ Tube

ቁልፉን ትቶ ዳቦውን?!
_____________
በምስሉ የምንመለከተው ሰው በታሰረበት ክፍል ሆኖ በፊቱ ሁለት አማራጮች ቀርበውለታል፤ አንድ ዳቦና የእስር ቤቱ በር መክፈቻ ቁልፍ። ሆኖም የእርሱ ምርጫ ለዘላቂው ከእስር ቤቱ የሚያወጣውን የበሩን ቁልፍ ሳይሆን ወቅታዊ ረሃቡን የሚያስታግስበትን ቁራሽ ዳቦ ማግኘት ሆኗል። ግን ለምን?

የብዙዎቻችንስ የምርጫ ዝንፈት ይሄው አይደለምን?! ለወቃታዊ ችግሮቻችን ፈጣን ማስታገሻ የሚሰጥ የሚመስለንን ቁራሽ "ዳቦ" ፍለጋ እንውተረተራለን እንጂ ዘላቂ መፍትሄ የሚቸረውን ቁልፍ (የእውቀት መክፈቻ) ለማግኘት እምብዛም እኮ አንተጋም። ከግብፅ የዘመናት እስራት ነፃ የወጡትን የእስራኤልን ልጆች ልብ ይሏል... ከምድረ በዳ ነፃነታቸው ይልቅ የግብፅ ሽንኩርት(የእስር ቤቱ ጥጋብ) ሲናፍቃቸው... ዘይገርም አሉ! ... ግን ለምን?

"ነፃነት" የሕይወት ወሳኝ እቅምና ውበት መሆኑን አለማወቅ አይመስላችሁም?

ስለዚህ ከውስጣዊና ውጫዊ እስራት ለዘላቂው ነፃ ከማያወጣ "የቁራሽ ዳቦ" ማስታገሻ ፍለጋ ፥ ነፍሳችንን አስገዝተንም ቢሆን እስከ ወዲያኛው አርነት ወደሚሰጠን የእውነት እውቀት "ቁልፍ" ፍለጋ ነፍሳችንን እናተጋ ዘንድ ይሁንልን እያልኩ ላብቃ።

#ነፃነት የሕይወት ወሳኝ አቅምና ውበት ነው!
---
Pastor abby
@nazrawi_tube