Get Mystery Box with random crypto!

ለእስራኤል እንደ ጠል እሆነዋለሁ! መንፈስ ቅዱስ ነፍስን ይመልሳል። የደረቀ ሕይወትን እንደ ገና | ናዝራዊ Tube

ለእስራኤል እንደ
ጠል እሆነዋለሁ!

መንፈስ ቅዱስ ነፍስን ይመልሳል። የደረቀ ሕይወትን እንደ ገና ሕያው ያደርጋል። ተስፋን ያለመልማል። የደከመን ጉልበት አበርትቶ ፍሬያማ ያደርጋል!
ዛሬ ማለዳ ያንን restoration/ renewal በሚናፍቅ ድባብ ዮሐንስ 7፥37-39 ላይ ያለውን ምንባብ እያነበብሁ ሳለሁ፥ መንፈሴ ወደ ሌሎች ክፍሎች ወሰደኝ።

በተለይ ልቤን እጅግ የነካው "ለእስራኤልም እንደ ጠል እሆነዋለሁ (I will be like a dew)፤ እንደ አበባም ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ሥሩን ይሰድዳል። ቅርንጫፎቹም ይዘረጋሉ፥ ውበቱም እንደ ወይራ፥ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ይሆናል።" (ሆሴ.14፥5-6) የሚለው ክፍል ነው። እንደ ጠል!

የእግዚአብሔር መንፈስ የሰውን መንፈስ ሕያው በማድረግ የታወቀ ነው። ግን አንድ ልዩ መስፈርት አለው። እሱም መጠማት ነው (ዮሐንስ 7፥37-39)። ቅዱስ ቃሉ "ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው ይጠግባሉና።" (ማቴ.5፥6) ብሏልና!
የእግዚአብሔር ጊዜ ነበርና ከላይ በቃሉ ውስጥ የተጠቀሱትን መንፈሳዊ ባርኮቶች እያሰብሁ ብዙ ተመሳሳይ ክፍሎችን አነበብሁ። እስቲ አራቱን ልጋብዛችሁ:-

➣"በተጠማ ላይ ውኃን በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈስሳለሁና፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አፈስሳለሁ፥ በፈሳሾችም አጠገብ እንደሚበቅሉ እንደ አኻያ ዛፎች በሣር መካከል ይበቅላሉ።" (ኢሳ.44፥3-4)፤

➣"ጕልበቴን ይያዝ፥ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ። በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ "በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።" (ኢሳ.27፥5-6)፤

➣"ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩት ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።....ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።" (ኢሳ.26፥9፣19)፤

➣"ዛፍ ቢቈረጥ ደግሞ ያቈጠቍጥ ዘንድ፥ ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው። ሥሩም በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥ ግንዱም በመሬት ውስጥ ቢሞት፥ ከውኃ ሽታ የተነሣ ያቈጠቍጣል፤ እንደ አትክልት ቅርንጫፍ ያወጣል።" ( ኢዮ.14፥7-9)!

መልካም ጊዜ ተባረኩልኝ!
Dr. Beke
@nazrawi_tube