Get Mystery Box with random crypto!

Here is another testimony … በአሜሪካ ምድር በኬንታኪ ግዛት የዊልሞር ከተማ በአ | ናዝራዊ Tube

Here is another testimony …

በአሜሪካ ምድር በኬንታኪ ግዛት የዊልሞር ከተማ በአስበሪ የቲዮሎጂ ዩኒቨርስቲ ውስጥ (Asbury Theological Seminary ,ky ) የነደደውን የመንፈስ ቅዱስ ጉብኝት ለመካፈል እኔ እና የምወደው ወዳጄና ጓደኛዬ 538mile 8ሰዓት ነድተን ከዚያ ደረስን።

በዚያ ስንደርስ ያየነውን ማመን አቃተን። ከቤተክርስቲያን ሕይወት ይልቅ ይህችን ብልጭልጭ ዓለም ወዶ ሄዷል ብለን የምናማው ወጣት ትውልድ የእግዚአብሔርን ጉብኝት ናፍቆ ከመሰብሰቢያ አዳራሽ ውጪ ስኪሪን ተተክሎ ተበርክኮ ሲፀልይ ፤ አጥንትን በሚሰብር ብርድ መሐል ቆሞ የጌታን ፍቅርና ታላቅነት እየጮኸ ሲዘምር። ከአንተ ውጪ ከክክብርህ ውጪ የምመኘው ነገር የለኝም እያለ ሲያውጅ። ኢየሱስ ስምህ ቅዱስ ነው፤ ስምህ ሕይወት ነው እያለ ከእንባ ጋር ጌታ ሲያወድስ በአይኔ እያየው ውስጤ ጌታን በመናፈቅ ተሞላ።

እግዚአብሔር የለም ተብሎ ሲማር ያደገ ወጣት እግዚአብሔር ሕያው ነው እያለ ሲመሰክር ሲታይ በእውነት ለባዖል ያልሰገዱ ቅሬታዎችን እግዚአብሔር ለራሱ ለይቷል አልኩኝ በልቤ።
ያንን ሁሉ ሠልፍ ተሰልፈን እዳይደርስ የለም ወደ አዳራሽ ውስጥ ለመግባት እድል ደረሰን። ከአዳራሹ ስንዘልቅ የጠበቅነው የቤተክርስቲያን ስነስርዓት በዚያ የለም። መባ የሚሰበስብ ሰው ለጌታ ስራ ስጦታ ስጡ ብሎ በሕዝቡ ጉሮሮ ላይ ቆሞ ጥቅስ እየጠቀሰ የሚያስገድድ ፓስተር ከምድረኩ ዝር አላለም።

ጊታራቸውን በአንገታቸው አንግተው በታላቅ ደስታ አንዴ በለሆሳስ፤ አንዴ በቀጭን ፤ አንዴ በወፍራም ድምፅ ያለ ምንም ግርግር ምንም አሙቁልኝ ሳይፈጥሩ ዜማ ከሆዳቸው የሚያፈልቁትን ዘማሪዎችን ሕዝቡ እየተከተለ ይዘምራል፤ ይጮኻል ፣ ያላቅሳል።

በዚህ ውስጥ ከቀዝቃዛው ወለል ላይ በጉልበታቸው ተበርክከው የጌታን ስም የሚጠሩና የሚያለቅሱ ወጣቶችን ሳይ በእውነት ጌታ በሥራ ላይ ነው አልኩኝ። በዚያ ፓስተሮች ከሕዝቡ ጋር ይፀልያሉ። እኔም በዚያ ካለ አንድ መጋቢ ጋር ተያይዘን አጥብቀን ፀለይን እና በመጨረሻ ስንበራረክ "He said we will meet in heaven" አለኝ ኤልትሪክ እንደያዘው ሰው አንዳች ነገር ውስጤ ነዘረኝ ዓይኖቼ በእንባ ተሞሉ እርሱም እያየሁት ማልቀስ ጀመረ ። እንደገና ተያይዘን ጌታ ሆይ ከበጉ ዙፋን የሚፈሰውን የሕይወት ውሃ ናፍቀናል ስምህን በእኛ ላይ ፃፍ እያልን እደገና ፀለይን ።

አንዳዶች የተነኩበትን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ከፍተው አይሰብኩም አያብራሩም ማንበብ ብቻ ። ጉባዔው አሜን ይላል ። እንደዚ ቆመው አንብበው ወደ መቀመጫቸው የሚመለሱ ብዙዎች ናቸው ። በዛው ውስጥ ጌታ በቃሉ ብዙዎችን ተናግሯል።

ኢየሱስን ጌትነት አምነው ክርስቶስን የነብሳቸው አዳኝ አድርገው የሚቀበሉም ብዙ ናቸው። ከክፉ ልምምድና ኃጢይት በንሰሃ የሚመለሱም ብዙዎች ናቸው።
ዝማሬው አይቆምም ባለ ጊታሮቹ ያለ አንዳች ድካም ይዘምራሉ እኛ ወዳ አዳራሹ ከ3ሰዓታት ሰልፍ ቡኻላ 4 pm ላይ ዘልቀን ከገባንበት ሰዓት ጀምሮ እስከ 11:30pm ድረስ ለ8 ሰዓታት ያለ መታከት የምስጋና የውዳሴ ፥ የአክብሮት የአድናቆት ዝማሬዎችን አሳርገዋል ። የእሁድ feb19 መርሃ ግብሩ የሚያበቃው 1am ላይ ነው ሰዓታችንን ስናይ መርሃ ግብሩ ሊፈፀም ቢበዛ 2ሰዓታት ቀርተውታል። እኔም ባልጀራዬም በረጅሞ የመገድ ጉዞ በረጅም ሰልፍ ተሰልፈን ስጋችን ስለደከመ የምናርፍበትን ማረፍያ ቤት ፍለጋ ጌታን እያበረክናና እያመሰገንን አዳራሹን ለቀን ወጣን።

በ Cincinnati Ohio በጣም የምወደው ወንድሜ Henok Tadese እና Helen Hailu ከቤታቸው ጣራ በታች በታላቅ እግድነት ተቀበለው ተከባክበው መገቡን። እኛም ከቅዱስ ቃሉ መግበን አፅናንተን ባርከን ፀልየን ተሰናበተን ወጣን። የጂፒኤስ ኮፖሳችን ወደ ቨርጂንያ አስተካክለን ሞልተን እየዘመርን እየፀለይን ስለ ተሀድሶ አስፈላጊነት እየተጫወትን ከቤታችን ደረስን። እኔም የሆነውን እና ያየሁትን ሁሉ እንዲ በፅሑፍ ለታሪክ ጫርኩት።

መጋቢ ተሊላ ፍቃዱ
@nazrawi_tube