Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ አውግስጢኖስ (354-430) በነገረ መለኮት እውቀቲ ትልቅ ተጽእኖን የፈጠረው (The mos | ናዝራዊ Tube

ቅዱስ አውግስጢኖስ (354-430)

በነገረ መለኮት እውቀቲ ትልቅ ተጽእኖን የፈጠረው (The most influential theologian ever!) ቅዱስ አውግስጢኖስ በ32 ዓመቱ በንግግር ጥበብ (Rhetoric፡-the art of effective or persuasive speaking or writing) የፕሮፌሰር ማዕረግ ያገኘ ሲሆን፣ በአፍላ የወጣትነት ፈተና መከራውን አይቷል፡፡ በልቡ ክርስቶስ እውነት እንደ ሆነና ከጋብቻ በፊት ወሲብ መፈጸም ደግሞ ልክ እንዳልሆነ ቢያውቅም፣ ያለ ወሲብ ሕይወት ምንም ጣዕም እንደሌለው ነበር የሚያስበው፡፡ በዚያ የሕሊና ግጭትም ከባድ ወቀሳ ነበረበትና እጅግ ብዙ ተቸግሯል፡፡ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ መሆኑን በመረዳቱም ራሱን እስኪጠላ ድረስ ይጨነቅ ነበር፡፡

አንዲት ልዩ ቀን በአስጨናቂ ሁኔታ በልቅሶ (ተማጽኖአዊ) ውስጥ እያለ ከአቅራቢያ ጎረቤት ያሉ ሕጻናት “አንሣና አንብበው አንሣና አንብበው” እያሉ ሲዘምሩ ሰማ፡፡ ወዲያው “ይህ መልእክት ከእግዚአብሔር ቢሆንስ?” ብሎ አስቦ የያዘውን መጽሐፍ ቅዱስ አንሥቶ ሲገልጠው፣ ሮሜ.13፥13-14 ላይ ያለውን መልእክት አገኘና አነበበው፡፡ ምንባቡ እንዲህ ነው የሚለው፡-“በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።”፡፡

መልእክቱን አንብቦ ሲጨርስ በሚገርም ሁኔታ ተለወጠ (At once, with the last words of this sentence, it was as if a light of relief from all anxiety flooded into my heart. All the shadows of doubts were dispelled.)፡፡

ከዚያ አስደናቂ ለውጥ በኋላ ቁርጠኛ ደቀ መዝሙር በመሆን ስለ ተጋ በአጭር ጊዜ እስከ ጵጵስና ማዕረግ የደረሰ የነገረ መለኮት ሊቅ ሲሆን፣ በብዙ መንፈሳዊ ነገሮች የክርስቲያን አማኞችን አስተሳሰብ የለወጠ የእምነት አርበኛ ነው (ከጌታ ኢየሱስና ከሐዋርያው ጳውሎስ ቀጥሎ ታላቅ ተጽእኖን የፈጠረ)፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራዎችን ለንባብ ያቀረበ ሲሆን፣ Confessions እና City of God እስከ አሁንም ድረስ እጅግ በጣም ተወዳጅና ተነባቢ ሥራዎቹ ናቸው፡፡ (Gerald R.McDermott, The Great Theologians, 49-62)

➢Faith is to believe what you do not see; the reward of this faith is to see what you believe.

➢Pray as though everything depended on God. Work as though everything depended on you.

➢If you believe what you like in the Gospel, and reject what you don't like, it is not the Gospel you believe, but yourself.

➢In order to discover the character of people we have only to observe what they love.

መልካም ቀን ተባረኩልኝ!
Dr. Beke
@nazrawi_tube