Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ክልል ክፍተኛ አመራሮች የልዑካን ቡድን በሰሜን አሜሪካ በኒውዮርክ ከተማ ከኢትዮጵያዊያንና | Natnael Mekonnen

የአማራ ክልል ክፍተኛ አመራሮች የልዑካን ቡድን በሰሜን አሜሪካ በኒውዮርክ ከተማ ከኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ውይይትና ምክክር አደረገ።

በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ የሚመራው የልዑክ ቡድን ኒውዮርክ ከተማ የሥራ ጉብኝት ቀጥሎ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሚሲዮን ጽሕፈት ቤት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ኢትዮጵታዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተወካዮች ጋር በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

የልዑክ ቡድኑ በሀገር ደረጃ እና ክልላዊ የልውጥ ጉዞ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሔ መንገዶች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱም ክልሉን ወደ ተሟላ ሰላም ለማምጣት መንግሥት እያደረገ ስላለው ጥረትና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየተደረገ ስላለው ጥረት ውይይት ተደርጓል። ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሚና በተመለከተ ውይይት ተደርጓል።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለክልሉ እና ለሀገራቸው ሰላም በጎ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ በሥራ እድል ፈጠራ እና ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ያሉ አማራጮችን በልዑክ ቡድኑ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ስለክልሉ የሰላም ሁኔታ፣ የልማት ሥራዎችና ድህነት ቅነሳ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ሥራን፣ የሀገራዊ አካታች የምክክር መድረክ ላይ የአማራ ክልል ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እየተከናወነ ያለውን ሥራ እና ለሥራ እድል ፈጠራ ያለውን ምቹ ሁኔታ በተመለከተ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

የልዑክ ቡድኑ አባላት በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሕግ ማስከበር ሥራው ያለበት ደረጃና ለሰላም እየተደረገ ያለውን ጥረት፣ የተጀማመሩ የልማት ሥራዎችን በተመለከተ፣ ተፈናቃዮችን ለመመለስ የተጀመረውን ሥራ እና እየገጠመ ያለውን ፈተና፣ የምክክር መደረኩን የሕዝባችንን ጥያቄዎች ለማስመለስ እየተሠራ ያለውን ሥራና ያለውን ተስፋ ለማስፋት ከግጭት አባባሽ ተግባራት ሁሉም ርቆ ወደ ተሟላና ክልሉን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ተግባራት ዙሪያ ለተሳታፊዎች አሥረድተዋል።

የልዑክ ቡድኑ የሥራ ጉዞ እንደቀጠለ ነው።