Get Mystery Box with random crypto!

በከተማዋ ለተከሰተዉ የነዳጅ ዕጥረት ምክንያቱ ጅቡቲ ላይ የደረሰ ከባድ ዝናብ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ከ | Natnael Mekonnen

በከተማዋ ለተከሰተዉ የነዳጅ ዕጥረት ምክንያቱ ጅቡቲ ላይ የደረሰ ከባድ ዝናብ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከሰሞኑ በመዲናዋ እየተስተዋለ ለሚገኘዉ የነዳጅ ዕጥረት ምክንያት ጅቡቲ ላይ ከባድ ዝናብ በመጣሉ ምክንያት የመንገድ መቆረጥ በማጋጠሙ መሆኑን ሰምተናል፡፡

በተጨማሪም አስቀድሞም ከቦታዉ በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እየተጫነ ባለመሆኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ለጣቢያችን ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር የቦርድ አባል አቶ ደሳለኝ አበባየሁ እንደነገሩን ከሆነ እነዚህ ምክንያቶች ከነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች የተነገራቸዉ ነዉ፡፡

ችግሩ ለመስተካከል ጊዜ ይወስድ እንደሆን የጠየቅናቸዉ አቶ ደሳለኝ‹‹ ጉዳዩ ትልቅ ነዉ፤ እንደ ቀላል የሚታይ አይደለም ያሉን ሲሆን፤ በእርግጠኝነት መንግስትም ሌት ተቀን ርብርብ አድርጎ ነገሮችን ያስተካክላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን›› ብለዉናል፡፡

ከጅቡቲ ከሚመጣዉ በተጨማሪ ክምችት ዉስጥ ነዳጅ አልነበረም ወይ ያልናቸዉ አቶ ደሳለኝ፤ ቤንዚን ከአዋሽ ፣ ከሱሉልታ ዲፖዎች ነዉ እየተጫነ ያለዉ ያሉን ሲሆን፤ አሁን ላይ ግን ከክምችት ለመጫን ያልፈለጉበት የራሳቸዉ ምክንያት ይኖራቸዋል ፤ መንግስትም ይህንን አይቶ መፍትሄ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን ብለዉናል፡፡

አንድ ያለን መንገድ የጅቡቲ ብቻ ነዉ፤ መንገዱ የተበላሸ በመሆኑ ደግሞ የመቆራረጥ ችግር ያጋጥማል ከባድ ዝናብ ሲዘንብ ደግሞ ችግሩን ከፍ ያደርገዋል ያሉት አቶ ደሳለኝ፤እንደዚህ ዓይነት ችግሮች የሚያግጥሙ በመሆኑ ለተወሰነ ጊዜ በትዕግስት ማለፍ አስፈላጊ ነዉ ብለዋል፡፡