Get Mystery Box with random crypto!

12 ማዳበሪያ አደገኛ ዕፅ በማዘዋወር ጥፋተኛ የተባለ የመንገዶች ባለስልጣን የመኪና ሹፌር በጽኑ እ | Natnael Mekonnen

12 ማዳበሪያ አደገኛ ዕፅ በማዘዋወር ጥፋተኛ የተባለ የመንገዶች ባለስልጣን የመኪና ሹፌር በጽኑ እስራት ተቀጣ

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የመኪና ሹፌር የሆነው ታምሩ ፍቅሩ የተባለ ተከሳሽ በታርጋ ቁጥር ኮድ 4 ኢት 15731 መኪና 12 ማዳበሪያ አደገኛ ዕፅ ሲያዘዋውር ተይዞ ጥፋተኛ መባሉን የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ተከሳሹ በሸገር ከተማ ልዩ ቦታው በተለምዶ ዓለምገና ተብሎ በሚጠራው የመኖሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ 12 ማዳበሪያ 280 ሺህ 50 ግራም የሚመዝን ካናቢስ የተባለ አደገኛ ዕፅ በተሸከርካሪ ውስጥ ይዞ መገኘቱ ተጠቁሟል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ችሎት አደገኛ ዕጾችን በማዘዋወር ወንጀል ተከሳሹን ያርማል በማለት በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ40 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።