Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከታጣቂዎች ጋር ለመነጋገር “የሰላም መንገድ” እንደሚያመቻች ገ | Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከታጣቂዎች ጋር ለመነጋገር “የሰላም መንገድ” እንደሚያመቻች ገለጸ

ከመንግሥት ጋር የትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ ታጣቂ ቡድኖች “ነፍጣቸውን ወደ ጎን አድርገው” ደኅንነታቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲነጋገሩ “የሰላም መንገድ” እንደሚያመቻች የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለጸ።

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን “ሁሉም አሸናፊ ይሆንበታል” ለሚለው ምክክር ከታጣቂ ኃይሎች ጋር የመነጋጋገር ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ ቢገልጽም፤ ለዚህ ውይይት ግን ታጣቂዎች ‘ነፍጥን ማስቀመጥ’ አለባቸው ብሏል።

ታጣቂዎች ነፍጣቸውን አውርደው ለመነጋገር ከመንግሥት ስጋት እንዳለባቸው ያነሳሉ ሲሉ የገለጹት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ፤ እስካሁን የኮሚሽኑን ጥሪ ተቀብለው የመጡ ታጣቂ ኃይሎች እንደሌሉ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ከታጣቂዎች ጋር ተገናኝቶ ለመነጋገርና ስጋቱን ለመቅረፍ “የሰላም መንገድ” (ደኅንነት ዋስትና) እንደሚያመቻች ፕ/ር መሥፍን ለቢቢሲ ተናግረዋል።