Get Mystery Box with random crypto!

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ቡራ ወረዳ | Natnael Mekonnen

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ቡራ ወረዳ ላይ ለሚገኙ ለክርስትያን ምዕመናኑ ፈጣን ምላሽ ሰጡ።

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቡራ ወረዳ በህብረተሰብ ተሳትፎ የፖሊስ ፅህፈት ቤት ለመገንባት የታቀደበት ስፍራ በአከባቢው በምትገኘዉ የህይወት ብርሀን ቤተክርስቲያንን ድንበር ይነካል የሚል ቅሬታ በቤተክርስቲያን መሪዎች እና ምዕመናን ተነስቶ ለክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ የቀረበ ሲሆን በትላንትናው እለት አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ እስከስፍራዉ ድረስ በአካል በመሄድ ለቤተክርስቲያኒቷ አፋጣኝ ምላሽ ሰቷል።

በትላንትናው እለት በተካሄደው ስነስርዓት ላይ የዞኑ እና የወረዳዉ አስተዳዳሪዎች ፣ የኢትዮጵያ ህይወት ብርሀን ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት ፣ የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች ፣ ምዕመናን በተገኙበት ሙሉ ለሙሉ የቤተክርስቲያኒቱን ችግር የተፈታ ሲሆን በቀጣይነት በመንግሥት እና በቤተክርስቲያኒቱ የሁሉቱን ህጋዊ ማንነት በማይጥስ መልኩ በአከባቢው በጋራ ትብብር በርከት ያሉ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ ቅሬታ ለመፍታት በተካሄደው መድረክ ላይ ተመላክቷል።

በዚህም አቶ አለማየሁ የፀጥታውን ዘርፍ እኛ በፖለቲካ ምህዳሮች የምንመራ ሲሆን ቤተክርስቲያኒቱ ደግሞ በፀሎት ታግዘን ዘንድ እንጠይቃለን ያሉ ሲሆን የፀጥታው ዘርፍ መጠናከር ለሁሉም አስፈላጊ ስለሆነ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመሆኑም ግንባታው ሊካሄድ የታሰበውን የፖሊሲ ፅ/ቤት ግንባታ ከመንግሥት እኩል የህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ክትትል እና ድጋፍ እንዲያደርግ ሃላፊው ጠይቀዋል።

በመጨረሻም ክብር አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን እና አባት የሃይማኖት መሪዎች ጉዳይ በህግ አግባብ በትግስት እንዲፈታ ስላደረጉ አመሰግነዋል።