Get Mystery Box with random crypto!

ዶክተር በሃይሉ ሀይሉ ከከፍታ ቦታ በመውደቅ በአካላቸው ላይ በተከሰተ ጉዳት ህይወታቸው ማለፉን የዳ | Natnael Mekonnen

ዶክተር በሃይሉ ሀይሉ ከከፍታ ቦታ በመውደቅ በአካላቸው ላይ በተከሰተ ጉዳት ህይወታቸው ማለፉን የዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ እንዳረጋገጠ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ስራውን የቀጠለ ሲሆን ከከፍታው የወደቁበትን ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ የምርመራ ውጤቶች ሲጠቃለሉ ለህዝብ ግልፅ እንደሚደረጉ አስታውቋል፡፡
***
የሰርጀሪ ህክምና ባለሞያ የሆኑት ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ ም በዕለተ እሁድ ሊነጋጋ ሲል ስፖርት ለመስራት ከቤት ወጥተው እንዳልተመለሱ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲገለፅ ቆይቷል።
ፖሊስ መረጃው ከደረሰው ሰዓት ጀምሮ ባደረገው ማጣራት የሟች ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ አስከሬን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሳሪስ አቦ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኝ ቀጠና 3 በተለምዶ ማሞ ድልድይ ስር ወድቆ በመገኘቱ በወቅቱ አስከሬኑ ተነስቶ የአሟሟታቸውን ምክንያት ለማወቅ ለአስክሬን ምርመራ ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል እዲሄድ ተደርጓል ፡፡ ከሆስፒታሉ የተገኘው የአስክሬን ምርመራ ውጤት እንደሚያስረዳው ከከፍታ ቦታ በመውደቅ በአካላቸው ላይ በተከሰተ ጉዳት ህይወታቸው ማለፉን የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ ይገልፃል፡፡ ሟች ዶ/ር በይሉ ሐይሉ ከከፍታው ላይ ቁልቁል ወደ ገደሉ በመውረድ አካላቸው ድንጋይ ላይ ስላረፈ በጭንቅላታቸው፤ በእግራቸው በጀርባ አጥንታቸውና በውስጥ የሰውነታቸው አካላት ላይ በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ከሆስፒታሉ የተገኘው የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ ያብራራል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ስራውን የቀጠለ ሲሆን ከከፍታው የወደቁበትን ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ የምርመራ ውጤቶች ሲጠቃለሉ ለህዝብ ግልፅ የሚደረጉ መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ፖሊስ በዶክተር በሃይሉ ሀይሉ አሟሟትን የተሰማውን ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ለሙያ አጋሮቻቸው መፅናናት እንዲሰጣቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡