Get Mystery Box with random crypto!

የጎጃም ኮማንድፖስት ትናንት በጎንጂ ቆለላ ፣ በገርገጭ ፣ በአጊታ ፣ በመርዓዊ እና በቲሊሊ ባደረገ | Natnael Mekonnen

የጎጃም ኮማንድፖስት ትናንት በጎንጂ ቆለላ ፣ በገርገጭ ፣ በአጊታ ፣ በመርዓዊ እና በቲሊሊ ባደረገው ማጽዳት የጽንፈኛው ሀይል ተመቷል ፤ የጦር መሳሪያም ተማርኳል ።

በሰሜን ጎጃም የተሰማራው ኮር በተለያዩ ቀጠናዎች  ባደረገው አሰሳና ፍተሻ በድምሩ 41 ጽንፈኛ ሲደመሰስ 11 ተማርኳል ። ስድስት ከሕዝብ የተዘረፉ ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ።

ሠራዊቱ ከአማራ ክልል የፀጥታ ሀይል ጋር በመቀናጀት በወሰደው ርምጃ ፣ በጎንጅ ቆለላ ዙሪያ 15 ፣ በገርጨጭ አራት ፤ በዜጋንታ ቀበሌ ላይ ዘጠኝ ተመቷል ።

በመርሀዊ አንድ የፅንፈኛ ታጣቂ ከነ ሙሉ ትጥቁ በቁጥጥር ስር ውሏል። በቲሊሊም ሦስት የፅንፈኛው አባላት ቆስለው በቁጥጥር ስር ውለዋል። የአዴት ከተማ ሚሊሺያና ፓሊስ አጊታ ከተማ የነበረውን ፅንፈኛ በማጥቃት 13 በመደምሰስ አራት ኤ ኬ ኤም እና ሌሎች መሳሪያዎች ተማርከዋል።

የ5ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ ወንድወሰን ጋሻው እንደተናገሩት ፣ የሕዝብን ሰላም ሲነሳ በነበረው ጽንፈኛ ላይ የተወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ ህብረተሰቡን ያስደሰተ ነው ።

ሠራዊቱ የቆመለትን ሕዝባዊ አላማ ከግብ አድርሶ ጎጃም ሰላም እስኪሠፍን ድረስ ጽንፈኛውን ከየተደበቀበት እያወጣን ለህግ ማቅረባችንን እንቀጥላለን ብለዋል።