Get Mystery Box with random crypto!

ክፍለጦሩ በሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን ዋዩ ወረዳ ለሚኖሩ ሶስት አሳዳጊ ለሌላቸው ህፃናት የገንዘብ ድጋፍ | Natnael Mekonnen

ክፍለጦሩ በሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን ዋዩ ወረዳ ለሚኖሩ ሶስት አሳዳጊ ለሌላቸው ህፃናት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ክፍለጦሩ በተሰማራበት የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ዋዩ ወረዳ የግዳጅ ቀጠና አሸባሪውን የኦነግ ሼኔ ቡድን በገባበት ገብቶ ከመምታትና ለህዝቦች ሰላምን ከማረጋገጥ ባሻገር አቅም ለሌላቸው እና አሳዳጊ ለሌላቸው ህፃናት የ160,255 ,00 /አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ አምስት ብር/ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።

በዕለቱ የተገኙት የክፍለጦሩ ዋና አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ተካ ተፈራ የክፍለጦሩ ሠራዊት ሰላም ጠል ለሆኑ አሸባሪ ሀይሎች አይቀጡ ቅጣት የሚቀጣ ፤ አቅም ላጡና ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው ወገኖች ደግሞ ካለው ቀንሶ የሚያጎርስ እና የሚደግፍ ህዝባዊ እና ልማታዊ ሰራዊት መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም ከግዳጃችን ጎን ለጎን ከማህበረሰቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት እና ሰላምን በማረጋገጥ የሰራዊታችንን እገዛ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ሁሉ ከጎናቸው መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ የክፍለጦሩ ስነ-ልቦና ግንባታ ቡድን መሪ ሻለቃ ቢኒያም አስገዶም እነዚህን መሰል ህዝባዊ ስራዎች እያደረገው የመጣና ቀጣይም የሚያደረገው የሰራዊታችን መገለጫ ከመሆኑም ባሻገር የተገነባበት ባህል እና እሴትም ጭምር መሆኑን አብራርተዋል።

የዋዩ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አቡሜ ኦብሳ  በበኩላቸው ሰራዊቱ ከህዝብ አብራክ የወጣ ህዝባዊ ሰራዊት ቢሆንም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ይህንን መሰል አስደናቂ በጎ ተግባር ያደርጋል ብለው እንዳልጠበቁና እንዳላሰቡ ገልፀው ለሰራዊቱ ትልቅ ክብርና ምስጋና አቅርበዋል።