Get Mystery Box with random crypto!

#ትግራይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፦ “ ጠላት ሊወረን ሲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር ፣ | Natnael Mekonnen

#ትግራይ

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፦

“ ጠላት ሊወረን ሲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር ፣ በሃይማኖት ፣ በፆታ ሳይለያይ የመሪውን ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክን ጥሪ በመቀበል ተሰባስቦ በመዝመት በነዚህ ተራሮች እና ኮረብታዎች ታሪክ እንዳልሰራ ሁሉ ለራሱ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ፤ ለአፍሪካ አህጉራችን እንዲሁም ለመላው የተጨቆነ ህዝብ ተስፋ የሰጠ ሳለ በዚህች መሬት፦
- ወንድም በወንድሙ ላይ ቃታ የሳበበት የተጋደለበት
- ንፁሃን የተገደሉበት
- ብዙዎች የተሰደዱበት
- በርካቶች በገዛ ሀገራቸው የተንከራተቱበት፣ የተፈናቀሉበት
- ንብረት የወደመበት
- #ሴቶች_የተደፈሩበት ሁኔታ ታሪክ ጅብዱ በተሰራበት ምድር እንዲያይ ያደረግነው። እነዚህ ተራራዎች ለዚህም እማኝ እንዲሆኑ ያደረግነው።

እነዚህ ተራሮች መናገር ቢችሉ እንዲነግሩን የምንፈልገው ግን የህዝባችንን ጀግንነት፣ ታሪክ ሰሪነት፣ አንድነት ነው፤ ምስክሮቻችን ናቸው።

በትግራይ ጦርነቱ እንደጀመረ ሰሞን መጥቼ ነበር። ከጦርነቱ ሁለት ወር በፊት እዚህ ነበርኩ። የጦርነት ደህና ገፅታ የለውም እጅግ አስከፊውን ግን አላየሁም ብዬ ነው የማስበው። “