Get Mystery Box with random crypto!

ህወሃት ያሥረከባቸው መሣሪያዎችን እና ተሽከርካሪዎችን የማንቀሳቀሱ ስራ ተጀመረ፡፡ በፌዴራል መንግ | Natnael Mekonnen

ህወሃት ያሥረከባቸው መሣሪያዎችን እና ተሽከርካሪዎችን የማንቀሳቀሱ ስራ ተጀመረ፡፡
በፌዴራል መንግስትና በህውሃት አመራሮች መካከል ደቡብ አፍሪካ እና ኬኒያ ላይ በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሠረት መከላከያ ሰራዊታችን የተረከባቸው የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና የጦር መሳሪያዎች ከቦታው መንቀሳቀስ ጀምረዋል።
ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም ከመቀሌ 36 ኪሎ ሜትር ርቀት ከሚገኘው አጉላ ካምፕ የአፍሪካ ወታደራዊ ታዛቢዎች በተገኙበት ህወሃት ያሥረከባቸው መሳሪያዎች ተሽከርካሪዎች እና ተተኳሾች ወደ ተዘገጀላቸው ቦታ በኮንቮይ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

ከመከላከያ ሎጄስቲክስ ዋና መምሪያ ኮሎኔል ነጋ መንገሻ በተደረሠው ስምምነት መሠረት ወታደራዊ ንብረቶቹን ተረከብን ከቦታው በማንሳት ወደ ተዘጋጀው ቦታ ጉዞ ጀምረናል ብለዋል፡፡

በቀጠናው የተሰማራው ሰራዊት አመራር ሌተናል ኮሎኔል አለሜ ታደለ ተቋማችን የሰጠንን ትህዛዝ በሚገባ ተገንዝበን ከህወሃት አመራሮች ጋር በመነጋገር ተሽከርካሪዎችን እና መሳሪያዎችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ መሰረት ተረክበን ለመከላከያ ሎጄስቲክስ ዋና መምሪያ አስረክበናል ንብረቶችን የማንቀሳቀስ ስራም ተጀምሯል ብለዋል።