Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ተኮር ተግባራቶቻችንን ለወገኖቻችን ማድረሳችንን፣አዲስ አበባን ደሃና ሃብታም በሚዛናዊነት የሚኖ | Natnael Mekonnen

ሰው ተኮር ተግባራቶቻችንን ለወገኖቻችን ማድረሳችንን፣አዲስ አበባን ደሃና ሃብታም በሚዛናዊነት የሚኖርባት የምትመች ማድረጋችንን ቀጥለናል።

ሰው ተኮር ተግባራት የዜጎቻችንን ጊዜያዊ ችግሮችና ፈታኝ ወቅቶች እንዲሻገሩ ከማገዙም ባሻገር፣ በእርግጥም ኢትዮጵያንና መጪውን ትውልድ በነባሩ የህዝባችን እሴት ላይ በጠንካራ የመተሳሰብና የአብሮነት መሰረት ላይ ለመገንባት ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡
ዛሬ በየካ ክፍለከተማ በርካታ በጎ አድራጊዎችን በማሳተፍ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተገንብተው የተጠናቀቁ የህዝብን ጥያቄ የሚመልሱና ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን አስመርቀናል፡፡
ከነዚህም ውስጥ፡-

-በከተማችን 14 ኛውን እስከ 1200 የሚደርሱ በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የማይችሉ ዜጎች የሚመገቡበት በሴንቸሪ ሞል ድጋፍ የተገነባ የምገባ ማዕከል።
-በቀን 600 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ያለዉና ለዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል የሚፈጥረው ሳሪድ ዳቦ ፋብሪካ ይገኙበታል።
በተጨማሪም አዲስ የተገነቡ የመማር ማስተማሩን ሂደት ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ የሁለተኛ እና የቅድመ መደበኛ ደረጃ ት/ቤት 60 የመማሪያ ክፍሎች እንዲሁም 120 ሱቆች ይገኙበታል፡፡
1200 የሚደርሱ ዜጎችን በየቀኑ ለመመገብ የተረከባችሁ አርሶአደሮች ፣በጎ ፍቃደኛ ባለሃብቶችላስተባበራችሁ እና ለመራችሁ አመራሮች፣ሰራተኞችና አንዲሁም መላው የክፍለከተማው ነዋሪዎች ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ!!

የሰሩ እጆች ይባረኩ!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧን አብዝቶ ይባርክ!!