Get Mystery Box with random crypto!

ግብፅ ለአራት ወር የሚሆን የስንዴ ክምችት እንዳላት አስታወቀች ግብፅ ለአራት ወራት የሚሆን የስ | Natnael Mekonnen

ግብፅ ለአራት ወር የሚሆን የስንዴ ክምችት እንዳላት አስታወቀች

ግብፅ ለአራት ወራት የሚሆን የስንዴ ክምችት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ አስታውቀዋል። ዩክሬን እና ሩሲያ በአለም ከፍተኛ የስንዴ አቅርቦት ፍላጎትን የሚሸፍኑ ሲሆን 80በመቶ ያህል ድርሻ አላቸው።

ሆኖም ግን ባለፈው የካቲት ወር ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ጦርነት መግባታቸውን ተከትሎ የምርት አቅርቦት መስተጓጎል እንዲፈጠር አድርጓል።ዩክሬን ውል ካሰረችው ምርቶች መካከል በከፊል ወደ ፖላንድ በባቡር ለማጓጓዝ ጥያቄ አቅርባ የነበረች ሲሆን ግብፅ የማጓጓዣ ወጪዬን በእጅጉ ይጨምራል ስትል አስታውቃለች።

ግብፅ ከህንድ 500,000 ቶን ስንዴ እየገዛች ቢሆንም የህንድ መንግስት ከተከፈለ የስንዴ ውል በስተቀር ወደ ውጭ ሀገራት ስንዴ እንዳይሸጥ ከልክሏል። በትላንትናው እለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ሩሲያ በዩክሬን ወደቦች ውስጥ የተከማቸ እህል ለውጭ ገበያ እስካልለቀቀች ድረስ በዩክሬን ያለው ጦርነት በአለም አቀፍ ደረጃ የምግብ እጥረት ስጋት እየጨመረ መሆኑን አስጠንቅቀዋል።