Get Mystery Box with random crypto!

‘’አዳዲስ አስተሳሰብና አሰራሮችን በመተግበር መከላከያ ሰራዊቱን በሁለገብ መልኩ ተጠቃሚ ለማድረግ | Natnael Mekonnen

‘’አዳዲስ አስተሳሰብና አሰራሮችን በመተግበር መከላከያ ሰራዊቱን በሁለገብ መልኩ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡’’ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር አብርሀም በላይ

#Ethiopia : የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ለሰራዊቱና ለሲቭል ሰራተኞቹ ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንት የዕጣ ማውጣትና የርክክብ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የመከላከያ ሚንስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ የመከላከያ ሰራዊታችንን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት ወደተግባር መገባቱን አረጋግጠዋል፡፡

ሀገርን በመስዋዕትነቱ እያስከበረ የሚገኘው ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችንን ተጠቃሚ ለማድረግ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ሚንስትሩ በጦርነት ውስጥ ሆነን ገንብተን ያጠናቀቅነውን የመኖሪያ ቤት ተቋሙን ላገለገሉ አባላት መተላለፉ አንዱ የለውጥ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜ/ጄ ኩምሳ ሻንቆ ፋውንዴሽኑ በኢንዱስትሪና በእርሻ ከመሰማራቱ በተጨማሪ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ውስጥ በስምንት ሳይቶች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት የሰራዊቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

በሰሚት ሁለት የጋራ መኖሪያ አፓርታማ ስለደረሳቸው መደሰታቸውን የገለጹት ሌ/ኮ ዘላለም ማሞ በቀሪ ዘመናቸው ሀገራቸውን ለማገልገል የበለጠ ተነሳሽነት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡

ሌላው ያነጋገርናቸው በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ለረጅም አመት አገልግገለው በጡረታ ላይ በመሆን በቤት ክራይ ይኖሩ የነበሩትና የእድሉ ተካፋይ የሆኑት ሻምበል መክብብ መኮንን ለረጅም ዘመን ያገለገልኩት ተቋም የቤት ባለቤት ስላደረገኝ ደስ ብሎኛል ብለዋል፡፡

በዕለቱ ሙሉ እድሳታቸው የተጠናቀቁ 529 ከባለአንድ እስከ ባለኣራት መኝታ ቤቶች ዕጣ ለወጣላቸው የሰራዊት አባላትና የሲቭል ሰራተኞች ተላልፏል፡፡