Get Mystery Box with random crypto!

የአያት መንደር ነዋሪዎች ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ እየፈረሰ ነው! በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ | Natnael Mekonnen

የአያት መንደር ነዋሪዎች ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ እየፈረሰ ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍል ከተማ አያት መንደር የዞን 8 ነዋሪዎች ሕጋዊ ካርታ አውጥተው ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ ያለ ምንም ማስጠንቀቂና ሕጋዊ ማስረጃ በትራክተር እየታረሰ መሆኑን ፓርኩን ያለሙት የመንደሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል ሲል አዲስ ማለዳ ዘግቧል፡፡

እንደነዋሪዎቹ ገለጻ ከሆነ ከ15 ዓመት በላይ ያለሙት የሕዝብ መናፈሻ ወይም ፓርክ ከነዋሪዎች በተዋጣ ገንዘብ በአረንጓዴ ልማት የተሸፈነ ነው፡፡

ይሁን እንጅ ዛሬ ማለዳ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘን ነው የመጣነው ያሉ ፖሊሶች ከ20 እስከ 30 የሚደርሱ ሰራተኞችና አንድ ትራክተር አሰማርተው ፓርኩን እያፈረሱ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ሕጋዊ ካርታ አውጥተው ከ15 በላይ በመናፈሻነት የተጠቀሙት ፓርክ እንደሚፈርስ ምን አይነት ማስጠንቀቂያም ይሁን መረጃ እንዳልተሰጣቸውም ጭምር ነው የተናገሩት፡፡

የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘን ነው የምናፈርሰው ያሉት የመንግሥት አካላት ማዘዣውን ለፓርኩ ባለቤት ለሆኑት ነዋሪዎች እንዲሳዩ ቢጠየቁም የፍርድ ቤት ማዘዣ ማሳየት አልቻሉም ተብሏል፡፡

Via Addis Maleda