Get Mystery Box with random crypto!

165 ተሽከርካሪዎች በትግራይ ክልል 3 ሺሕ ቶን ምግብ አከፋፈሉ!! የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባለ | Natnael Mekonnen

165 ተሽከርካሪዎች በትግራይ ክልል 3 ሺሕ ቶን ምግብ አከፋፈሉ!!

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ 165 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል ደርሰው 3 ሺሕ ቶን ምግብ ማከፋፈሉን አስታወቀ፡፡

የምግብ አቅርቦቱ 120 ሺሕ ዜጎችን ተደራሽ ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡ 3 ሺሕ 4 መቶ ቶን የምግብ እርዳታ ደግሞ ወደ ማከፋፈያ ጣቢያዎች መላካቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም አሁን ላይ እርዳታ የጫኑ 94 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እያቀኑ ነው ተብሏል፡፡ የምግብ እርዳታ ስርጭቱ በአፋር እና በአማራ ክልልም በሂደት ላይ መሆኑን የዓለም የምግብ ፕሮግራም በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ገልጿል።