Get Mystery Box with random crypto!

በቀጣይ 5 ዓመት 60 በመቶ የሚሆነውን የመድሀኒትና የህክምና ግብዓት በሀገር ውስጥ ምርት ይሟላል | Natnael Mekonnen

በቀጣይ 5 ዓመት 60 በመቶ የሚሆነውን የመድሀኒትና የህክምና ግብዓት በሀገር ውስጥ ምርት ይሟላል ተባለ።

በቀጣይ አምስት አመታት 60 በመቶ የመድኃኒት እና የህክምና ግብዓትን በሃገር ውስጥ ምርት እናሟላለን ሲሉ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍን በአዲስ ምዕራፍ ለማጠናከር ከፋርማሲዩቲካል አምራቾች እና ባለድርሻ አካላት ጋር እየተደረገ ባለው ምክክር መድረክ ነው።