Get Mystery Box with random crypto!

አላህን መፍራት ┄┄┉┉✽‌»‌ »‌✽‌┉┉┄┄ (ክፍል 1) •┈• ❁ •┈ | ነሲሐ ለሱኒዋ እህቴ !!

አላህን መፍራት
┄┄┉┉✽‌»‌ »‌✽‌┉┉┄┄

(ክፍል 1)
•┈• ❁ •┈•

አላህን መፍራት (ኸውፍ ሚናሏህ) የዒባዳ ፍሬና አላማውም ጭምር ነው። ተቅዋ (አላህን መፍራት) በአንድ ሠውና በአላህ ቁጣ መካከል የሚኖር መከላከያ ነው። ይህ እንዲሆን የሚያደርገው ደግሞ ትክክለኛ የአላህ ፍራቻ ነው።

يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمْ وَاخْشَوْا يَوْمًا لَا يَجْزِي وَالِدٌ عَنْ وَلَدِهِ وَلَا مَوْلُودٌ هُوَ جَازٍ عَنْ وَالِدِهِ شَيْئًا إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا وَلَا يَغُرَّنَّكُمْ بِاللَّهِ الْغَرُورُ
“እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ። ወላጅም ከልጁ (በምንም) የማይጠቅምበትን፤ ተወላጅም እርሱ ወላጅን በምንም ጠቃሚ የማይሆንበትን ቀን ፍሩ። የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና። ቅርቢቱም ሕይወት አትሸንግላችሁ። በአላህም (መታገስ) አታላዩ (ሰይጣን) አያታልላችሁ።” ( ሉቅማን 31፤33)

ቁርአንም ሆነ ሐዲሶች በማስጠንቀቅያ እንዲሁም ስለዕለት ቂያማና ስለሑኔታዎቿ በሚተርኩ አንቀፆች የተሞሉ ናቸው።

فَاعْبُدُوا مَا شِئْتُمْ مِنْ دُونِهِ قُلْ إِنَّ الْخَاسِرِينَ الَّذِينَ خَسِرُوا أَنْفُسَهُمْ وَأَهْلِيهِمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَلَا ذَٰلِكَ هُوَ الْخُسْرَانُ الْمُبِينُ لَهُمْ مِنْ فَوْقِهِمْ ظُلَلٌ مِنَ النَّارِ وَمِنْ تَحْتِهِمْ ظُلَلٌ ذَٰلِكَ يُخَوِّفُ اللَّهُ بِهِ عِبَادَهُ يَا عِبَادِ فَاتَّقُونِ
“ከእርሱ ሌላ የሻችሁትን ተገዙ። ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በትንሣኤ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው” በላቸው። ለእነርሱ ከበላያቸው ከእሳት የኾኑ (ድርብርብ) ጥላዎች አልሏቸው። ከበታቻቸውም ጥላዎች አልሏቸው። ይህ አላህ ባሮቹን (እንዲጠነቀቁ) በእርሱ ያስፈራራበታል። “ባሮቼ ሆይ! ስለዚህ ፍሩኝ።” (አል-ዙመር 39፤15-16)

ረሡል /ሰ.ዐ.ወ/ መጨረሻችን እንዳያስጠላ እንዲህ ያስጠነቅቁናል፡-

فوالله الذي لا إله غيره إن أحدكم ليعمل بعمل أهل الجنة حتى ما يكون بينه وبينها إلا ذراع فيسبق عليه الكتاب فيعمل بعمل أهل النار فيدخلها وإن أحدكم ليعمل بعمل أهل النار حتى ما يكون بينه وبينها إلا ذراع فيسبق عليه الكتاب فيعمل بعمل أهل الجنة فيدخلها متفق عليه

“ከሱ ውጪ ሌላ ጌታ የሌለ በሆነው አላህ ይሁንብኝ አንደኛችሁ የጀነት ሠዎችን ስራ ይሰራና ለሞት አንድ ክንድ ያህል ሲቀረው የተደነገገው ይቀድመዋል ከዚያም የእሳት ሠዎችን ስራ ይሰራና እሳት ይገባል። አንድኛችሁ የእሳት ሰዎችን ስራ እየሰራ ይቆይና ለመሞት አንድ ክንድ ሲቀረው የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል” ( ቡኻሪና ሙስሊም)

በሌላ ሃዲስ ረሡል (ሰ.ዐ.ወ) አንዲህም ብለዋል:-

والله لو تعلمون ما أعلم لضحكتم قليلاً ولبكيتم كثيرًا وما تلذذتم بالنساء على الفرش ولخرجتم إلى الصعدات تجأرون إلى الله تعالى) رواه الترمذي(

“በአላህ ይሁንብኝ የማውቀውን ብታውቅ ኖሮ ትንሽ ስቃችሁ ብዙ ባለቀሳችሁ ነበር። እንዳችሁም በአልጋ ላይ ጨዋታ ደስተኛ አይሆንም ነበር። (ከዚህ ይልቅ) ወደ ሜዳዎች ወጥታችሁ ወደ አላህ አቤት ትሉ ነበር። ( ቲርሚዚ)

በሌላ ዘገባም

شيبتني هود وأخواتها) رواه الترمذي

“ሁድና አምሳያዎቹ አሸበቱኝ” ( ቲርሚዚ)

እንዲሁም

ما وجدت منظرًا إلا والقبر أفظع منه

“እንደቀብር ያለ አስደንጋጭ ቦታ የትም አምሳያውን አላገኘሁለትም!”

ዑመር አንድ ቀን በጣም አለቀሱ:: በዚሁ ለቅሷቸውም ለህመም ተዳርገው ሰዎች ጠየቋቸው። ነገር ግን ለለቅሶና ለህመም የዳረጋቸው ሌላ ሳይሆን

إِنَّ عَذَابَ رَبِّكَ لَوَاقِعٌ
“የጌታህ ቅጣት በእርግጥ ወዳቂ ነው፤ (የማይቀር ነው)።” ( አጥ-ጡር 52፤7) የሚለውን የቁርአን አንቀፅ በማዳመጣቸው ነበር።

አላህን የመፍራት ፍሬዎች
•═══••• •••═══•

1.አላህን መፍራት ዕውቀት ለማግኘት ትልቁ መሳሪያ ነው።

إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ
“አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው። አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው።” ( ፋጢር 35፤28)

ይህ ጌታውን ተገዥ የሆነ አዋቂ ባህሪይ ነው። ይህ አዋቂ የጌታውን ደረጃ በዕውቀቱ አማካኝነት አውቆ እሱን ይፈራዋል፣ ይጠነቀቀዋልም።

2.አላህን መፍራት የሰው ልጅ ባህሪይ ብቻ ሳይሆን የመላኢኮችም ነው።

يَخَافُونَ رَبَّهُمْ مِنْ فَوْقِهِمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ
“ጌታቸውን ከበላያቸው ሲኾን ይፈሩታል። የታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ።” ( አን-ነሕል 16፤50)

3.አላህን መፍራት፣ ስራቸውን ለአላህ ብቻ ያደረጉ የዳዕዋ ሰዎች መገለጫ ነው።

الَّذِينَ يُبَلِّغُونَ رِسَالَاتِ اللَّهِ وَيَخْشَوْنَهُ وَلَا يَخْشَوْنَ أَحَدًا إِلَّا اللَّهَ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ حَسِيبًا
“ለእነዚያ የአላህን መልእክቶች ለሚያደርሱና ለሚፈሩት ከአላህ በስተቀርም አንድንም ለማይፈሩት (ተደነገገ)። ተቆጣጣሪም በአላህ በቃ።” ( አል-አሕዛብ 33፤39)

4.አላህን መፍራት፣ የሙዕሚኖች ምልክትና መታወቂያ ነው


إِنَّمَا ذَٰلِكُمُ الشَّيْطَانُ يُخَوِّفُ أَوْلِيَاءَهُ فَلَا تَخَافُوهُمْ وَخَافُونِ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ
“እንዲህ የሚላችሁ ሰይጣን ብቻ ነው። ወዳጆቹን ያስፈራራችኋል። አትፍሩዋቸውም። ምእምናንም እንደኾናችሁ ፍሩኝ።” ( ኣሊ-ዒምራን 3፤175)

የአላህ ፈሪዎች ሁሉ አለቃ ረሡል (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፡-

أنا أعلمكم بالله وأشدكم له خشية

“እኔ አላህን እጅግ በጣም አዋቂና ፈሪ ነኝ”

ይ'ቀ'ጥ'ላ'ል'★ـ{ـــــــــــــــــــــ ـــــــــــــــــــــ}ـ★