Get Mystery Box with random crypto!

ይህ የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ታላቅ ምክር ነው። አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ | ነሲሐ ለሱኒዋ እህቴ !!

ይህ የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ታላቅ ምክር ነው።

አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጋ መጣና "ለዱንያም ሆነ ለአኼራ የሚጠቅም ንግግር ለመጠየቅ መጣው" አላቸው ።
እሳቸውም ደግሞ "የመጣልህን ጠይቅ"
አሉት።

"ከሰው ሁሉ አዋቂ ለመሆን እፈልጋለው?"
እሳቸውም "አላህን ፍራ" አሉት

"ከሰው ሁሉ ሀብታመ ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው።
"ባለህ ነገር ተብቃቅተ አላህን አመስግን" አሉት

"ትክክለኛ ፈራጅ እና ታማኝ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል
"ለራስህ የምትወደውን ለሰዎች ውደድ"
አሉት።

"ከሰው ሁሉ ብርቱ ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል
"በአላህ ተወከል"አሉት

"በአላህ ዘንድ ብቸኛ ተመራጭ ለመሆን
እፈልጋለው" ሲላቸው?
"ዚክር አብዛ" አሉት።

"ከሰው ሁሉ በላጭ ለመሆን እና ጥሩ ሰው ለመሆን
እፈልጋለው?" ሲል
"ለሰው ጠቃሚ ሁን" አሉት።

"የተከበረና ቸር ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው
"ችግርህን ለፍጡር አትንገር" አሉት።

"ረሱል እና አላህ እንዲወዱኝ እፈልጋለው?" ሲል
"አንተም እነሱ የወደዱትን
ውደድ" አሉት::

"ከወንጀል የጠራው ሁኜ አላህንመገናኘት እፈልጋለው" ሲል
"ጀናባህን በደንብ ታጥበ እስቲግፋር አብዛ ማልቀስ መተናነስ መታመም
አለብህ" አሉት።

"ከበጎ ሰሪወች ለመሆን እፈልጋለው"
ሲላቸውም
"አላህን ልክ እንደምታየው ሁነክ ተገዛው" አሉት።

"ኢማኔ እንዲ ሞላ
እፈልጋለው" ሲል
"ፀባይህን አሳምር" አሉት።

"እርዝቄ እንዲሰፋ እፈልጋለው" ሲል
"ተዋዱዕ አዘውትር" አሉት።

"ዱዓዬ ሙስተጃብ እንዲሆንልኝ እፈልጋለው?" ሲላቸው
"ሀራም አትብላ" አሉት::

"አላህን ከሚታዘዙ ሰዎች ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል
"ግዴታዎችህን ፈፅም" አሉት።

"በአላህ ዘንድ ትልቁ ሀሠና ወይም ደግ ሥራ የቱ ነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው
"መልካም ፀባይ መተናነስ እና በበላ ላይ ሰብር ማድረግ ነው" አሉት።

"በአላህ ዘንድ የትኛው ስርዓት ነው መጥፎ ሥራ?" ሲል ሲጠይቃቸው
"መጥፎ ፀባይና ፍላጎትን መከተል ናቸው" አሉት

"በዱንያም ሆነ በአኼራ የአላህን ቁጣ የሚያበርድ ምንድነው" ሲል ጠየቃቸው?
"ድብቅ ሰደቃ እና ዘርን መቀጠል ናቸው" አሉት።

"የቂያማ ቀን በአላህ ኑር ለመሰብሰብ
እፈልጋለው?" ሲል
"ሰውን አትበድል" አሉት

"የቂያማ እለት አላህ እንዲያዝንልኝ እፈልጋለው?"
"ለአላህ ባርያዎች እዘን" አሉት።

"የቂያማ ቀን የጀሀነም እሳት የሚያጠፋው ምንድነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው
"በችግር ላይ ወይም በሙሲባ ላይ ትህግስት መሰድረግ ነው" አሉት።

"የቂያማ እለት ነውሬ እንዲሸፈንልኝ እፈልጋለው?" ሲል
"የወንድምህን አይብ ሸፍን" አሉት።

"የቂያማ ቀን ከአላህ ቁጣ ሰላም ለመሆን
እፈልጋለው?" ሲል
"በአንድም ፍጡር አትቆጣ" አሉት።