Get Mystery Box with random crypto!

#እጅግ በጣም ጥሩ ሰው ነህ በመሰረቱ መልካም ሰው ነህ፡፡ ታማኝ ፣ ጨዋ ፣ ሀቀኛ እና ታታሪ ነህ | Nur-Africa Academy Education/ ኑር–አፍሪካ አካዳሚ ትምህርት

#እጅግ በጣም ጥሩ ሰው ነህ

በመሰረቱ መልካም ሰው ነህ፡፡ ታማኝ ፣ ጨዋ ፣ ሀቀኛ እና ታታሪ ነህ፡፡ ሰዎችን ከልብህ አክብረህ በትህትና የምታስተናግድ ነህ፡፡ ለቤተሰብህ፣ ለወዳጆችህ ፣ እንዲሁም ለምትሰራበት ኩባንያ ጊዜህን እና ጉልበትህን ሳተሰስት የምትሰጥ ነህ፡፡ ጠንካራ ፣ በራሱ የሚተማመን እና ኃላፊነት የሚሰማው በጎ ሰው ነህ፡፡ አዋቂ ፣ ብልህና በልምድ የካበትክ ነህ፡፡ የምታስፈልገው በቅርብህ ላሉት ብቻ ሳይሆን ለምትኖርበት ማህበረሰብም ጭምር ነው፡፡ የተወለድከው ለልዩ ምክንያት ነው፣ የምታሟላው ትልቅ እጣ ፈንታ አለህ፡፡ በሁሉም መንገድ እጅግ በጣም ጥሩ ሰው ነህ፡፡

ከላይ የሠፈረው አንቀጽ የእውነተኛ ማንነትህና ባህሪህ መግለጫ ቃል ነው፡፡ ሁሉንም ጊዜ የሠፈረው አንቀጽ አይገልጽህ ይሆናል ነገር ግን የውስጣዊ ማንነትህን እና በሕይወትህ የምታደርገው ጉዞን የሚያሳይ ጥሩ አጠቃላይ መግለጫ ነው፡፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የእውነትም ዋጋ ያለውና ጠቃሚ ሰው መሆንህን አምነህ ስትቀበል በንግግርህና በድርጊትህ ሁሉ ትገልጸዋለህ፡፡ በጊዜ ሂደትም እውነት ይሆንልሃል፡፡ በሀሳብ ደረጃ የያዝከውም በገሀድ ያለ እውነትህ ይሆናል፡፡ ስለዚህ “እራሴን እውደዋለሁ፤ እራሴን አፈቅረዋለሁ፡፡ በመሰረቱ በሁሉም መንገድ መልካም ሰው ነኝ፤ በምሞክረው ነገር ላይ ሁሉ ሁልጊዜም የምችለውን አደርጋለሁ” የሚሉ ቃላቶችን ለራስህ ደጋግመህ ንገረው፡፡

#የስኬት አቦጊዳ