2022-07-28 17:35:12
የ ኬሎ ሚዲያን ቃለመጠይቅ ሰምተን አንጀታችን ቅቤ ጠጣ
ትናንት ጊዜ ስላልነበረኝ አልሰማሁትም ነበር አሁን ቃለመጠይቁን አደመጥኩት።
ጋዜጠኛው እዚሁ ፌስቡክ እና ቴሌግራም ላይ አሉባልተኞች የሚፈተፍቱትን የመንደር ወሬ ለቃቅሞ አምጥቶ ጃዋር የ WBO እና የኦሮሞ ትግል ጠላት እንደሆነ አድርጎ ይጠይቀዋል
ከዛም አርቲስት ሙክታር ኡስማን ጃዋር የቱ ጋር ነው የ WBOን ስም የጠራው ? እስቲ አንተ ጃዋርን ለመተቸት ትክክለኛ ማስረጃ ከያዝክ አቅርብልኝ እና እንወያይበት ፣ እዚ ሚዲያ ላይ የመንደር አሉባልታ እየለቃቀምክ መጥተህ ህዝብን አታደናግር ።ኦሮሞ አንድነቱን መጠበቅ አለበት ይህ አይነት በህብ መሀል አልቱባልታ ለቆ ህዝብን መከፋፈል በ 1983 ራሱ ተሞክሮ የነበረ ነው። እስቲ ማስረጃህን አምጣ ጃዋርን ከሀዲ ያደረክበት ? እኔ እስከማውቀው ድረስ በቀለ ገርባ ራሱ እኛም መንገዶች በዚህ ከቀጠሉ እና አፈናው ከቀጠለ ወደ ትጥቅ መግባታችን አይቀርም ነው ያለው። ብሎ ሲያፋጥጠው
ጋዜጠኛው ላብ በላብ ሆኖ በየሚዲያው የሚወራ ነገር ነው ብሏ ለመከራከር ሲሞክር
ሙክታር ቀጥሎ ወሬ ለቃቅመህ ነው እንዴ እዚህ ህዝብን የምትከፋለው ? ጃዋር ኦሮሞን የከዳበትን ማስረጃ ማቅረብ ከቻልክ አቅርብ ካልሆነ ስም የማጠልሸት ፕሮፓጋንዳ አልቀበልም ይለዋል
ጋዜጠኛው የሚለው ነገር ጠፍቶት አንገቱን አቀርቅሮ ዝም አለ
ሙክታር አቦ ይመችህ
............................................
አንዳንዶች ደግሞ በዚህ ጋዜጠኛ ጎጠኝነት ምክንያት ኬሎ ሚዲያን ለማንቋሸሽ የምትሄዱበት መንገድ ተገቢ አይደለም። ሚዲያው የኦሮሞ ህዝብ ሚዲያ ነው ይህ አስተሳሰብ ጋዜጠኛውን እንጂ ሚዲያውን እንደማይወክል 100% ግልፅ ነው።
@my_oromia
3.5K views14:35