Get Mystery Box with random crypto!

🍌ባናና ሙዚቃ🎶የሙዚቃ ግጥሞች ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ musziqahiwote_lyrics — 🍌ባናና ሙዚቃ🎶የሙዚቃ ግጥሞች ™
የቴሌግራም ቻናል አርማ musziqahiwote_lyrics — 🍌ባናና ሙዚቃ🎶የሙዚቃ ግጥሞች ™
የሰርጥ አድራሻ: @musziqahiwote_lyrics
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.69K
የሰርጥ መግለጫ

🇪🇹 የዘፈን ዓለም 🌍

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-02-24 14:04:38 አርቲስት: አብነት አጎናፍር
#_ማነው ያለው

ማነው ያለው አልልም አልጠይቅም፣
ማነው ያለው ብዬም አልጨነቅም፣
ማነው ያለው ምን አሉኝ ደግሞ ብዬ፣
ላልቆም ነገር ከመንገድ ከጉዞዬ።
ማነው ያለው ብዬ እኔ ሰው አልወቅስም፣
ማነው ያለው ውስጤን ላያውቀው ማንም፣
ማነው ያለው ስቆ ማለፍ መተው ነው፣
የሚያኖርም የሰራም ደግ አባት ነው።
አአአአአአይይይ
ለማን ብዬ ባዶነት ለሞላው፥
ለማን ብዬ ለገለባው ክብሬ፣
ለማን ብዬ ካበደው ጋር ልበድ፥
ለማን ብዬ ከጠፋው አብሬ፣
ለማን ብዬ እልህ ተጋብቼ፥
ጨካኝ ልሁን መራራቴን ትቼ።
ለማን ብዬ ባልተረጋገጠ፣
ለማን ብዬ መሬት ባረገጠ፣
ለማን ብዬ በደለበ ወሬ፣
ለማን ብዬ በወለደ በሬ፣
ለማን ብዬ ስጦታው ሰላሜን፣
ለማን ብዬ ልነጠቅ ደስታዬን።
ማነው ያለው ካልኩኝ ብዙ እሰማለሁ፣
ማነው ያለው ብልስ ማንን አምናለሁ፣
ማነው ያለው አውቀዋለሁ ባይ ብዙ፣
በሞላበት ያደክማል ጓዝ መዘዙ።
እ እ እ እ እህ እህ . . . እ እ እ እ እህ እህ . . .
እራስን ክቦ ለክብር ዝና፣
ይራመዳል ሰው በሰው ጎዳና፣
ሞልቶ ላይሞላ ለሽንቁር ኑሮ፣
እንዴት ይገፋል ይሄ ተጨምሮ፣
ሰው ለቁርሱ እጁን አጣጥፎ፣
ጫፍ ይዞ መሄድ ሆዱን ታቅፎ፣
ላላዩት እውነት አሉ ላይረባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ቢዋል ሳታምን ግባ።
አአአአአአይይይ…ምምምም
ማነው ያለው አልልም አልጠይቅም፣
ማነው ያለው ብዬም አልጨነቅም፣
ማነው ያለው ምን አሉኝ ደግሞ ብዬ፣
ላልቆም ነገር ከመንገድ ከጉዞዬ።
ማነው ያለው ብዬ እኔ ሰው አልወቅስም፣
ማነው ያለው ውስጤን ላያውቀው ማንም፣
ማነው ያለው ስቆ ማለፍ መተው ነው፣
የሚያኖርህ የሰራም ደግ አባት ነው።
እ እ እ እ እህ እህ . . . እ እ እ እ እህ እህ . .
ለማን ብዬ አለኝ ያሉት በምድር፣
ለማን ብዬ ፈጥኖ ለሚያሳፍር፣
ለማን ብዬ ከዘመኔ ስፍር፣
ለማን ብዬ ቅንጣት ለማልጨምር፣
ለማን ብዬ ወዳጅ ላፍራ ብዬ፣
የሰው ላድንቅ የኔን ቀን ገድዬ።
ለማን ብዬ ቃላት ከማይመርጠው፥
ለማን ብዬ ለከት ካጣ አንደበት፣
ለማን ብዬ ከማይጠቅም ምክር፥
ለማን ብዬ እርግማን ካለበት፣
ለማን ብዬ የኮኮብ ድምቀቴን፣
ለማን ብዬ ላጥፋው ማንነቴን።
ማነው ያለው ካልኩኝ ብዙ እሰማለሁ፣
ማነው ያለው ብልስ ማንን አምናለሁ፣
ማነው ያለው አውቀዋለሁ ባይ ብዙ፣
በሞላበት ያደክማል ጓዝ መዘዙ።
እ እ እ እ እህ እህ . . . እ እ እ እ እህ እህ . . .
እራስን ክቦ ለክብር ዝና፣
ይራመዳል ሰው በሰው ጎዳና፣
ሞልቶ ላይሞላ ለሽንቁር ኑሮ፣
እንዴት ይገፋል ይህ ተጨምሮ፣
ሰው ለቁርሱ እጁን አጣጥፎ፣
ጫፍ ይዞ መሄድ ሆዱን ታቅፎ፣
ላላዩት እውነት አሉ ላይረባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
ሲነግሩህ ቢዋል ሳታምን ግባ።
ሲነግሩህ ውለው ሳትሰማ ግባ፣
አሉ ተባለን ሳታምን ግባ።
እ እ እ እ እህ እህ . . .

Join
https://t.me/joinchat/U74a12ayrXpK_aSM
12.0K views11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-24 14:01:29
10.3K views11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-24 13:51:39
እዮብ_መኮንን
# የጋበዝኳቸው
ወጣው ከ እልፍኜ ቆምኩኝ ከበሩ
የጋበዝኳቸው ሁሉም ቢቀሩ
እንባ እንዳጋቱ ሁለቱ አይኖቼ
መንገድ ስጀምር ድግሱን ትቼ
(አሀሀ ታራንታንታራ አሀሀ ታራንታንታራ)(2x)
ከጥሪው መዝገብ ስምሽ ሳይሰፍር
በሌሎች ግብዣ አመጣሽ ፍቅር
(አሀሀ ታራንታንታራ አሀሀ ታራንታንታራ)(2x)
ከጥሪው መዝገብ ስምሽ ሳይሰፍር
በሌሎች ግብዣ አመጣሽ ፍቅር
አክባሪ ያጣው ደጋሽ እልፍኜ
ያልታለምሽውን አንቺን አገኘ
በምድር ይሁን ወይስ ከሰማይ
ኬት መምጣትሽን ባይኔ ሳላይ
ድንገት ፊቴ ተከስተሽ አስደነቅሽኝ
ልቤን ገዝተሽ(2x)
አሀሀ ሃይሎጋ ካንቺጋ(4x)
ወጣው ከ እልፍኜ ቆምኩኝ ከበሩ
የጋበዝኳቸው ሁሉም ቢቀሩ
እንባ እንዳጋቱ ሁለቱ አይኖቼ
መንገድ ስጀምር ድግሱን ትቼ
(አሀሀ ታራንታንታራ አሀሀ ታራንታንታራ)(2x)
ከጥሪው መዝገብ ስምሽ ሳይሰፍር
በሌሎች ግብዣ አመጣሽ ፍቅር
(አሀሀ ታራንታንታራ አሀሀ ታራንታንታራ)(2x)
ከጥሪው መዝገብ ስምሽ ሳይሰፍር
በሌሎች ግብዣ አመጣሽ ፍቅር
አክባሪ ያጣው ደጋሽ እልፍኜ
ያልታለምሽውን አንቺን አገኘ
በምድር ይሁን ወይስ ከሰማይ
ኬት መምጣትሽን ባይኔ ሳላይ
ድንገት ፊቴ ተከስተሽ አስደነቅሽኝ
ልቤን ገዝተሽ(2x)
አሀሀ ሃይሎጋ ካንቺጋ(6x)
አሀሀ ሀይሎጋ
አሀሀ ሀይሎጋ.....

@Fiker_ma
10.4K viewsedited  10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-24 12:59:54
#Meek1_One
#ሸግዬ_ሸጊቱ

ስምል ባንቺ ስምል በሄድኩበት ቦታ
ትንሽ አይደል ትልቅ የማገኘው ደስታ
ስምል ባንቺ እኔስ ስምል በሄድኩበት ቦታ
ትንሽ አይደል ትልቅ ሁሌም የማገኘው ደስታ
አዬ ወይ ነዶ
ልቤ ያንቺን ፍቅር ተላምዶ
አዬ ወይ ነዶ
ልቤ ያንቺን ፍቅር ተላምዶ
እኔ የወደድኳት
እሷ የጠላቺኝ
እኔ የወደድኳት
እሷ የጠላቺኝ
ስማዳ ስማዳ
ስማዳ ገባቺኝ
ስማዳ ስማዳ
ስማዳ ገባቺኝ አዬ


ሸግዬ ሸጊቱ
የሴት እመቤት
ከመልክም አንደኛ
መልከ-መልካሚት አዬ
የቀሚስሽ ጥለት
ብዙ ነው አይነቱ
ያንቺስ የብቻው ነው
ጠላትሽ መብዛቱ

በዝቶ ሰው በዝቶ
አየነው ዝናሽን
በዝቶ ሰው በዝቶ
ሰው ገዳይ መሆንሽን
በዝቶ ሰው በዝቶ
አየነው ዝናሽን
በዝቶ ሰው በዝቶ
ሰው ገዳይ መሆንሽን

በይ ነይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ንገሪኝ
በይ ነይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ንገሪኝ አዬ


እኔ የወደድኳት
እሷ የጠላቺኝ
እኔ የወደድኳት
እሷ የጠላቺኝ
ስማዳ ስማዳ
ስማዳ ገባቺኝ
ስማዳ ስማዳ
ስማዳ ገባቺኝ አዬ


ወንጀለኛ ልባል
ባንቺ ይክሰሱኝ
ስሜም ባንቺ ይጥፋ
የሷ ካስባለኝ
አልኩኝ ብድግ ብድግ
ዘንድሮስ ቀለለኝ
አንጀቴን አውጥተሽ
በላሽው መሰለኝ
እንደታሪክ ሳወራ
አልሰለች ስምሽን ስጠራ
እንደታሪክ ሳወራ
አልሰለች ስምሽን ስጠራ

ፍቅርሽ ከኔ ሆኖ
ዘወትር አርበኛ
ቀልቤን እየገዛው
አርጎኛል ምርኮኛ
በይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ድገሚኝ ሳሚኝ
በይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ድገሚኝ ሳሚኝ
በይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ድገሚኝ ሳሚኝ
በይ ነይ ነይ ነይ ውድዬ
በይ ድገሚኝ ሳሚኝ

ተው ተው ሲሉኝ የኔን ፍላጎት
ዘውድ አይሉ ጎፈር ምርጫ እንደሰጡት
ተው ተው ሲሉኝ የኔን ፍላጎት
ዘውድ አይሉ ጎፈር ምርጫ እንደሰጡት
አዬ
አሃ
@Fiker_ma
9.8K viewsedited  09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-24 12:42:47 › ጂጂ
› ትናገር አድዋ



የሰው ልጅ ክብሩ
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቶል ሰው ሊያድን
ሰውን ሲያከብር
በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ
በክብር ይሄዳል ሰው ሊኖር
ሰው ሞቶ

የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት
ሰው ተከፍሎበታል
ከደም እና ከአጥንት

ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ ትናገር ትመስክር
ትናገር አድዋ ትናገር ሀገሬ
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታቹ ዛሬ

በኩራት
በክብር
በደስታ
በፍቅር

በድል እኖራለው ያው በቀን በቀን
በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን

አድዋ ዛሬናት አድዋ ትናንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለነሱ ለአደዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች

የ ጥቁር ድል አንባ አድዋ
አፍሪካ እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ
እእእእ ተናገሪ...

°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°





•════••• •••════•

@Fiker_ma
8.7K viewsedited  09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-24 12:42:19 › ዳዊት ፅጌ
› ደስ አለኝ

•════••• •••════•

ኧረ እንዴት ነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
የምን ሳቅ ጨዋታ ደግ ተሸኝቶ
ቀየውም መንደሩም ተክዞ ሰንበቶ
እምም የተፈጥሮም ነገር የውበትም ነገር
እምም አንቺን ናፍቆ መዋል አንቺን ናፍቆ ማደር
ኧረ እንዴት ነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
ኧረ እንዴት ነ... ሽ
እህምምም
ደስ አለኝ እመጣለሁ ስትይ ሰምተዋል መሰለኝ
ደስ አለኝ ዘማመሩ ወፎቹ ዜማቸው ደስ አለኝ
እመጣለሁ ስትይ ሰምተዋል መሰለኝ ደስ አለኝ
ዘማመሩ ወፎቹ ዜማቸው ደሳለኝ
የአበቦቹ ድምቀት አቤት ውበታቸው
ከደጃፌ ደርሰሽ እስክታስንቂቸው
ድንጉላው ተነሳ እንጀራውን ትቶ
ሊቀስምሽ መሰለኝ መምጣትሽን ሰምቶ
አቤ... ት አቤት አቤት አቤት
ኧረ ፈኩ ፈኩ አበቦች ከመስኩ
ለመለሙ ወፎች ተሳሳሙ
ዘማመሩ ዜማቸው ደስ አለኝ
መምጣትሽን ሰምተዋል መሰለኝ
አሀሀ
አፈረች ጀምበሯም አፈረች
አፈረች አይንሽን እያየች
እያየች ተመኘች ደጄ ተቀምጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
እያየች ተመኘች ደጄ ተቀምጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
አፈረች ጀምበሯም አፈረች
አፈረች አይንሽን እያየች
እያየች ተመኘች ደጄ ተቀምጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
እያየች ተመኘች ደጄ ተቀምጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
አንቺ ስትመጪ ልትሞቅሽ ብትወጣ
ኧረ እንዴት ነሽ
እህህህህ
ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነሽ
ኧረ እንዴት ነሽ


°°°
°°°
°°°
°°°
°°°




•════••• •••════•

@Fiker_ma
8.4K viewsedited  09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-24 12:41:53 › ዳዊት ፅጌ
› ደግሞ በዚህ ላይ

•════••• •••════•

ወርቅ አልማዝ ብልሽ ይገልፅሻል ወይ
ዉድ እንቁ ብልሽ ይገልፅሻል ወይ
ስም አጣሁልሽ የኔ ስጦታ
መቼም ልዩ አርጎ ፈጥሮሻል ጌታ
ስም አጣሁልሽ የኔ ስጦታ
ሁሉን ሙሉ አርጎ ፈጥሮሻል ጌታ

የሚገርመኝ አይንሽን ሳይ
ያጥብያ ኮኮብ ነሽ መልከ ፀሐይ
ደሞ ሲመሽ ጀምበር ጠልቃ
ትፈኪያለሽ እንደ ጨረቃ
እንደ ጨረቃ ፈክቶ
መልክሽ ሲያበራ መሽቶ
የሰውነትሽ ቅኔ
ግርም ይለኛል እኔ
አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አቤት...
አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አ ...
ደሞ በዚ ላይ ፀባይ
ደሞ በዚ ላይ ዉበት
ደሞ በዚ ላይ .
ደሞ በዚ ላይ ...
አቤት አቤት አቤት

ወርቅ አልማዝ ብልሽ ይገልፅሻል ወይ
ዉድ እንቁ ብልሽ ይገልፅሻል ወይ
ስም አጣሁልሽ የኔ ስጦታ
መቼም ልዩ አርጎ ፈጥሮሻል ጌታ
ስም አጣሁልሽ የኔ ስጦታ
ሁሉን ሙሉ አርጎ ፈጥሮሻል ጌታ

የቁንጅና ዉብ ምሳሌዋ
ደሞ እንዳንቺ ማነው ጨዋ
አቻሽ ጠፋኝ በዚዓለም ላይ
ቸር ደግ አርጎሽ ከሰው በላይ
አልመስልሽም እንቁ
ልብሽ ነው ለኔ ብርቁ
ማን ብዬ ልጥራሽ እኔ
ቃል አጣሁልሽ ቅኔ
አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አቤት...
አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አ ...

ደሞ በዚ ላይ ፀባይ
ደሞ በዚ ላይ ዉበት
ደሞ በዚ ላይ .
ደሞ በዚ ላይ ...

አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አቤት...
አ...
ደሞ በዚ ላይ
ዉበት
ደሞ በዚ ላይ
እ...
ደሞ በዚ ላይ
አ ...
ደሞ በዚ ላይ ፀባይ
ደሞ በዚ ላይ ዉበት
ደሞ በዚ ላይ .
ደሞ በዚ ላይ ...
አቤት አቤት አቤት
ደሞ በዚ ላይ .
ደሞ በዚ ላይ ...
ደሞ በዚ ላይ .
ደሞ በዚ ላይ ...

°°°
°°°




•════••• •••════•

@Fiker_ma
8.2K viewsedited  09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-24 12:41:23 › ዳዊት ፅጌ
› ደሀ አይጣላ ከውሃ

•════••• •••════•

አንዲት ሴት ነበረች የቤት ሰራተኛ
ቀን ስትደክም ውላ ሌትም የማተኛ
ኑሮዋ ሆነና የአርባ ቀን እድሏ
ልጅ እያጠባች ነው የተለያት ባሏ
ላንድ ልጇ ስትል በነፃ እየሰራች
ደሞዟን ሳትል ነው ለፍታ ያሳደገች
እንደወጣ ቢቀር ያ ባሏ ያ ጎበዝ
ስትረግም ትኖራለች ያሻገረውን ወንዝ
ለራሷ ምትቀምሰው ምትልሰው ሳይኖራት
ምን ለታጠባ ነው የምትወልደው ሲሏት
ልጅ ስጦታ አይደለም ከመጣ በኃላ
ብላ ተስፋ ቆርጣ ሄደች አገር ጥላ
አገር ጥላ ጠፍታ ተሰዳ በሩቁ
ትኑር ትሙት እንኳን አንዳቸው ሳያውቁ
ስንት ዘመን አልፎ ናፍቃ ብትመለስ
ይሄው ፊት አስነሳት የታቀፈቺው ነፍስ
ምናለ ብተወው የባሏን እሮሮ
ያሻገረውን ወንዝ መርገም በንጉርጉሮ
ወንዙን አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
እሷም አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
ካገር አገር ስትዞር ተሸክማ ጕዟን
ስንት አሳር አይታለች ለማሳደግ ልጇን
እርፍት እንኳን ሳታውቅ በነፃ እየሰራች
ወዟን አራግፋ ነው ለፍታ ያሳደገች
ታዲያ አንድ ቀን ጠዋት ማለዳ ተነስታ
ቅጠል ለቅማ መጣ ሳታርፍ እንኳ ላፍታ
ልጇን ባንቀልባ አዝላ ውሃ ልትቀዳ
ከለመደቺው ወንዝ መሸት ሲል ወርዳ
ጎንበስ ባለችበት በድካም ስሜቷ
አመለጣት ልጇ አይ እድሏ ህብቷ
ደራሽ ወሰደባት የት ገባ ፀሎቷ
የምትወደው ልጇ ሆነ የውሃ ሽታ
ምን ያደርግላታል ብታለቅስ ብትረግመው
ከውሃ ተጣልታ የትም ለማትደርሰው
እሷም አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
እሷም አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ ድሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
አይ ደሃ ...
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ ድሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ
ደሃ ...
አይጣላ ከውሃ

°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°





•════••• •••════•

@Fiker_ma
7.8K viewsedited  09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-24 12:41:06 › ዳዊት ፅጌ
› እትቱ

•════••• •••════•

እትቱ እትቱ በረደኝ
እትቱ በቀን በፀሀይ
እትቱ ናፍቆትሽ ክረምቱ
እትቱ ይዞት ገባ ወይ
ዛሬስ ዛሬስ ከዓይኔ ባጣሽ
ዛሬስ ድንገት በማርፈድሽ
ዛሬስ ላምባዬን አንስቼ
ወጣሁኝ ወጣሁ ልፈልግሽ
ዛሬስ ወጣሁ ልፈልግሽ

እትቱ እትቱ በረደኝ
እትቱ በቀን በፀሀይ
እትቱ ናፍቆትሽ ክረምቱ
እትቱ ይዞት ገባ ወይ

ዛሬስ ስፍስፍ አልኩኝ ባንቺ
ዛሬስ ሰውነቴም ከዳኝ
ዛሬስ በልቤ አለ ነገር
በሰው በሰው አፍ ላይዳኝ
ዛሬስ በሰው አፍ ላይዳኝ

በቀን መብራት ይዤ ተቆጠርኩ እንደ ጅል
እኔስ ባንቺ ጉዳይ በል ፈጠን አልከጅል
ሳልምሽ አምሽቼ ሲናፍቅሽ አይኔ
አንቺን ካላገኘው መንጋቱስ ለምኔ ዋ
የጨዋታሽ ማማር የሳቅሽ ፏፏቴ
ውሃውን አስረሳኝ ሲፈስ ወደ አንጀቴ
ወንዙ ዳር አጥምቂኝ መልክሽ ይታየኛል
አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል
አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል
በወግ ያልነኩትን ዘራፍ ሲሉት ሸሽቶ
ይታገለኝ ጀመር ፍቅርሽ ጦር አንስቶ
አንቺው ምከሪልኝ ዘንጉን ይመልሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
አቤት አቤት አቤት ሃሃሃ
አቤት አቤት አቤት ሃ...

°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°





•════••• •••════•

@Fiker_ma
7.6K viewsedited  09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-24 12:40:45 › ዳዊት ፅጌ
› ባየው ባየው

•════••• •••════•

አይንሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
አይንሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
መልክሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
መልክሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
እንዲህ ውብ ተፈጥሮን የታደለ ማነው?
አይንሽን አልሰለችህ አለኝ ባየው
የገላሽን ማማር የሰራ አካልሽን
የአይን አገላለጥሽ ያሰባበርሽን
እንዲህ ውብ ተፈጥሮን የታደለ ማነው?
አይንሽን አልሰለችህ አለኝ ባየው
ሆድዬ ተይ አውጊኝ ምሽቱ ሳይነጋ
ልቤ እንዲረጋጋ
ሆድዬ ተይ አውጊኝ ምሽቱ ሳይነጋ
ልቤ እንዲረጋጋ
አንቺዬ ከነጋማ ወዲያ ብርሀን ነው
ተይ አውጊኝ ገና ነው
አንቺዬ ከነጋማ ወዲያ ብርሀን ነው
ተይ አውጊኝ ገና ነው
ከነጋማ ወዲያ
ፀሀይ ከደመቀ
ምንም ሳላወጋሽ
ለሊቱ ካለቀ
ኋላ ብትናፍቂኝ ተጠያቂው ማነው?
አይንሽን ቀን ከሌት
አልሰለችህ አለኝ ባየው
አይንሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
አይንሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
መልክሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
መልክሽን ባየው ባየው አልሰለችህ አለኝ ባየው
እንዲህ ውብ ተፈጥሮን የታደለ ማነው?
አይንሽን አልሰለችህ አለኝ ባየው
ማየቱንስ ያያል
ሁሉም እንደህልሙ
ያንቺ ግን ይለያል
ብዙ ነው ትርጉሙ
ይሄን ውብ ተፈጥሮ
የተረዳው ማነው?
አይንሽን አልሰለችህ አለኝ ባየው
ሆድዬ ፈገግታሽ የጥዋት ጮራ ነው
አለም ሚሞቀው
ሆድዬ ፈገግታሽ የጥዋት ጮራ ነው
አለም ሚሞቀው
አንቺዬ የልቤን ለልብሽ ልንገረው
እይታሽ ፈራጅ ነው
አንቺዬ የልቤን ለልብሽ ልንገረው
እይታሽ ፈራጅ ነው
በአይኖችሽ ብርሀን ደምቆ በፈገግታሽ
የዘላለም ፍቅሩን
አሜን ነው የሚልሽ
ይሄን ታላቅ ውበት
የተረዳው ማነው?
አይንሽን ቀን ከሌት
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው(አይንሽን)
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው(ጥርስሽን)
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው(አይንሽን)
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው(ጥርስሽን)
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው
አልሰለችህ አለኝ ባየው
ባየው ባየው ባየው
አልሰለችህ አለኝ ባየው

°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°





•════••• •••════•

@Fiker_ma
7.4K viewsedited  09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ