Get Mystery Box with random crypto!

› ዳዊት ፅጌ › እትቱ •════••• •••════• እትቱ እትቱ በረደኝ እትቱ በቀን በፀሀይ | 🍌ባናና ሙዚቃ🎶የሙዚቃ ግጥሞች ™

› ዳዊት ፅጌ
› እትቱ

•════••• •••════•

እትቱ እትቱ በረደኝ
እትቱ በቀን በፀሀይ
እትቱ ናፍቆትሽ ክረምቱ
እትቱ ይዞት ገባ ወይ
ዛሬስ ዛሬስ ከዓይኔ ባጣሽ
ዛሬስ ድንገት በማርፈድሽ
ዛሬስ ላምባዬን አንስቼ
ወጣሁኝ ወጣሁ ልፈልግሽ
ዛሬስ ወጣሁ ልፈልግሽ

እትቱ እትቱ በረደኝ
እትቱ በቀን በፀሀይ
እትቱ ናፍቆትሽ ክረምቱ
እትቱ ይዞት ገባ ወይ

ዛሬስ ስፍስፍ አልኩኝ ባንቺ
ዛሬስ ሰውነቴም ከዳኝ
ዛሬስ በልቤ አለ ነገር
በሰው በሰው አፍ ላይዳኝ
ዛሬስ በሰው አፍ ላይዳኝ

በቀን መብራት ይዤ ተቆጠርኩ እንደ ጅል
እኔስ ባንቺ ጉዳይ በል ፈጠን አልከጅል
ሳልምሽ አምሽቼ ሲናፍቅሽ አይኔ
አንቺን ካላገኘው መንጋቱስ ለምኔ ዋ
የጨዋታሽ ማማር የሳቅሽ ፏፏቴ
ውሃውን አስረሳኝ ሲፈስ ወደ አንጀቴ
ወንዙ ዳር አጥምቂኝ መልክሽ ይታየኛል
አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል
አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል
በወግ ያልነኩትን ዘራፍ ሲሉት ሸሽቶ
ይታገለኝ ጀመር ፍቅርሽ ጦር አንስቶ
አንቺው ምከሪልኝ ዘንጉን ይመልሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
አቤት አቤት አቤት ሃሃሃ
አቤት አቤት አቤት ሃ...

°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°
°°°





•════••• •••════•

@Fiker_ma