Get Mystery Box with random crypto!

ዘካ የሌለባቸው ንብረቶች ~ ① ለንግድ ሳይሆን ለቤት ፍጆታ የተቀመጡ ንብረቶች (ሸቀጣ ሸቀጥ፣ ምግ | Muslim Students

ዘካ የሌለባቸው ንብረቶች
~
① ለንግድ ሳይሆን ለቤት ፍጆታ የተቀመጡ ንብረቶች (ሸቀጣ ሸቀጥ፣ ምግቦች፣ እህሎች፣ መገልገያ ቁሳቁስ፣ መገልገያ እንስሳት፣ ለሽያጭ ያልቀረቡ አልባሳት) ዘካ የለባቸውም።

② ለሽያጭ ሳይሆን ለኪራይ የተዘጋጁ ቤቶች፣ መኪናዎች፣ ማሽኖች፣ ወዘተ በራሳቸው ዘካ የለባቸውም። ዘካ የሚመለከታቸው ከኪራይ የተሰበሰበው ገንዘብ ለዘካ መጠን ደርሶ አመት ከሞላው ነው።

③ ከወርቅና ብር ውጭ ያሉ ማእድኖች (አልማዝ፣ ፕላቲነም፣ ውድ የሆኑ የድንጋይ አይነቶች፣ …) በራሳቸው ዘካ የለባቸውም። ለንግድ ከዋሉ ግን እንደማንኛውም የንግድ ሸቀጥ ዘካ ይመለከታቸዋል።

④ የህዝብ ማመላለሻና የጭነት መኪኖች በገቢያቸው እንጂ በራሳቸው ዘካ የለባቸውም። የሚያስገቡት ገቢ ለዘካ መጠን ከደረሰ በኋላ አመት ከሞላው የአጠቃላዩን 2•5% ዘካ ይወጣል። [መጅሙዑል ፈታዋ፣ ኢብኑ ባዝ: 14/181] [አልለጅነት አድዳኢማህ: 9/349]

⑥ ለሽያጭ ወይም ለአገልግሎት መሆን አለመሆኑን በቁርጥ ያልተወሰነበት ቤት ወይም መኪና ዘካ የለበትም።

⑦ ተበዳሪው ችግረኛ በመሆኑ ወይም የሚያጉላላ በመሆኑ ይመለሳል ተብሎ ተስፋ የማይጣልበት ብድር ዘካ አይወጣበትም።

ማሳሰቢያ
-----------
* ብድሩ ተመልሶ ድንገት እጅ ከገባና ለዘካ መጠን የደረሰ ከሆነ እጅ ከገባበት ጊዜ አንስቶ አመት ሲሞላው ዘካው ይወጣል።
* ብድሩ ቢጠይቅ የሚያገኘው አይነት ከሆነ እጁ ባይገባም ዘካ ይመለከተዋል።
* በጊዜ የተገደበ ብድር ከሆነ (ለምሳሌ የዛሬን አመት እከፍላለሁ ቢለው) ጊዜው እስከሚደርስ ዘካ አይመለከተውም። ወላሁ አዕለም።
=
( Ibnu Munewor ፣ ሚያዚያ 21/2013)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor