Get Mystery Box with random crypto!

አልሀምዱሊላህ ያረብ። ለረጅም ወራት 'ያ አላህ ለረመዷን አድርሰን' ስ | Muslim Students

አልሀምዱሊላህ ያረብ።

ለረጅም ወራት "ያ አላህ ለረመዷን አድርሰን" ስንል ነበር እነሆ በራሕመቱ ለረመዷን አድርሶናል አልሃምዱሊላህ ።

አሁን ዱዓችን ሊሆን የሚገባው
"ያረብ መልካም ስራዎችን ወፍቀን አግራልንም ስራችንም ተቀበለን"

በረመዷን ወር ዋና ዋና ከሚባሉ መልካም ስራዎች ውስጥ

⓵)) ፆም ዋናውና ትልቁ ነው
⓶)) ሰላት ፈርዱም ሱናውም
➂))ቁርኣን
➃))ዱዓ
➄/))ሰደቃ( ፆመኛን ማስፈጠርም ጭምር ።

እነዚህንና ሌሎችንም አላህ የሚወዳቸው ስራዎችን እናብዛ።

ዋናው ነገር ረመዷንን ማግኘቱ ሳይሆን በርሱ መጠቀሙ ነውና ።እንጠቀምበት ካለፈ በኋላ መጸጸቱ አይጠቅመንምና ከአሁኑ ከሚያዘናጉን ነገሮች እንራቅ።

አላህ ሆይ ! መጾም ላልቻሉ ቤተሠቦቻችን አንተ እዘንላቸዉ መቻሉንም ስጣቸዉ ያረብ


@Muslimstudentsgroup