Get Mystery Box with random crypto!

#የሰላምታ_ትሩፋትና #ሰላምታን_ማብዛት_ስለመታዘዙ   #ክፍል_2 አላህ እንዲህ ብሏል፦ “በሰላ | Muslim Students

#የሰላምታ_ትሩፋትና #ሰላምታን_ማብዛት_ስለመታዘዙ  
#ክፍል_2

አላህ እንዲህ ብሏል፦
“በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ ይበልጥ ባማረ (ሰላምታ) አክብሩ፤ ወይም (እርሷኑ) መልሷት፡፡” (አን ኒሳእ፡ 86)

#ሐዲሥ 131 / 846

አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፦ “አላህ አደምን በፈጠረ ጊዜ ‘ለነዚያ _ለተቀመጡት መላእክት_ ሰላምታ አቅርብላቸው። ምላሻቸውንም በጥሞና ስማ። ያንተና የዝሪያዎችህ ሰላምታ ነውና’ አለው። ‘አስሰላሙ ዐለይኩም’ አላቸው። ‘አስሰላሙ ዐለይከ ወረሐመቱላሂ’ በማለት <<ወረሕመቱላህ>> የሚል አክለው መለሱለት፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም)

  ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ “አስሰላሙ ዐለይኩም” የሚለው ቃል ኢስላማዊ የሰላምታ አቀራረብ ስልት ነው። አላህ ይህን ቃል አደምን ከፈጠረበት ዕለት አንስቶ ለባሮቹ ሰላምታ አድርጎታል።
2/ ሰላምታ ሲመልሱ በርከት አድርጎ መመለስ በላጭ መሆኑን ሐዲሡ ያሳያል። “አስሰላሙ ዐለይኩም” ላለ “ወዐለይኩሙ ሰላም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ” በማለት ማከል በላጭ ነው።