Get Mystery Box with random crypto!

Muslims Ummah 🌍

የቴሌግራም ቻናል አርማ muslims_ummahh — Muslims Ummah 🌍 M
የቴሌግራም ቻናል አርማ muslims_ummahh — Muslims Ummah 🌍
የሰርጥ አድራሻ: @muslims_ummahh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 168
የሰርጥ መግለጫ

يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۖ لَهُ ٱلْمُلْكُ وَلَهُ ٱلْحَمْدُ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ قَدِيرٌ
በሰማያት ውስጥ ያለው በምድርም ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ ያሞግሳል፡፡ ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ለእርሱ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-21 10:59:46 ከ3000 በላይ የሙዕጂዛ_ባለቤት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ሙሀመድ ጨረቃ ለሁለት የተከፈለለት ነብይ
ሙሀመድ ከጣቶቹ መሃል ውሃ የፈለቀለት ነብይ
ሙሀመድ የታላቁ ሙዕጂዛ የቁርአን ባለቤት የሆነ ነብይ
ሙሀመድ ወደሱ ግመል እያለቀሰ በመምጣት የበደል ስሞታ ያቀረበለት ነብይ
ሙሀመድ ደረቅ እንጨት በሱ ናፍቆት ያለቀሰለት ነብይ
ሙሀመድ ተኩላ የአላህ መልዕክተኛ መሆኑን የመሰከረለት ነብይ
ሙሀመድ ዛፍ መሬት እየቀደደች ወደሱ በመምጣት መልዕክተኝነቱን የመሰከረችለት ነበይ
ሙሀመድ በጦርነት ምክንያት የወጣችን የቀታዳን አይን ወደቦታው የመለሰለት ነበይ
ሙሀመድ የታላቁ ምልጃ ባለቤት የሆነ ነብይ
ሙሀመድ የቀብር ሰዎች ዋይታ ይሰማው የነበረ ነበይ
ሙሀመድ የኢስራእና የሚዕራጅ ባለቤት የሆነ ነብይ
ሙሀመድ ሁሉንም አንቢያዎች በበይተል መቅዲስ ኢማም ሆኖ ያሰገደ ነብይ
ሙሀመድ ጀነትና ጀሃነምን በአይኑ ያየ ነብይ
ሙሀመድ የኡሁድ ተራራ የተንቀጠቀጠለት በኋላም "ተረጋጋ" ብለው እግሩን ሲያሳርፍበት የተረጋጋለት ነብይ
ሙሀመድ ምግብ በእጃቸው ላይ ሆኖ ተስቢህ የሚያደርግለት ነብይ
ሙሀመድ ድንጋዩም ዛፉም ሰላምታ የሚያቀርብለት ነበይ
ሙሀመድ እሳቸውን በመግደል ሴራ የተመረዘው ስጋ እንዳይበሉት የተመረዘ መሆኑን በመናገር ራሱን ያጋለጠለት ነበይ
ሙሀመድ ለእርድ የቀረቡ ስድስት ግመሎች ቅድሚያ በሱ እጅ ለመታረድ የተሽቀዳደሙለት ነብይ
ሙሀመድ አይነስውር ሰውየ በነገሩት የተወሱል ዱዓ አይኑን ያበራለት ነብይ
ሙሀመድ በበድር ዘመቻ ጊዜ ከውጊያ በፊት የእያንዳንዱን ሙሽሪክ መውደቂያ(መገደያ) ቦታ " እገሌ እዚህ ቦታ ይወድቃል እገሌ እዚህ ቦታ ይገደላል" በማለት ቀድሞ የተናገረ በኋላም ሳይዛነፍ እንዳለው የሆነለት ነብይ
ሙሀመድ ከፊቱ እንደሚያየው ከኋላውም የሚያይ ነብይ
ሙሀመድ ላቡ ከሚስክ የበለጠ መአዛ የነበረው ነብይ
ሙሀመድ ለዛቱ ጥላ የሌለው ነብይ
ሙሀመድ ትንሽ መጠጥና ምግብ በሱ በረካ እጅግ በርካታ ሰውና ሰራዊት ያጠግብለት የነበረ ነብይ
ሙሀመድ ድምፁ ማንም ሊያደርስበት በማይችልበት ቦታ ላይ የሚደርስለት ነብይ
ሙሀመድ በዘመቻ ላይ የመላኢካ ወታደሮች ኑስራ(እርዳታ) የሚያደርግለት ነብይ
ሙሀመድ የሱ ዳበሳ በረከት የሆነለት ነብይ (ለምሳሌ በሀንዞላ እንደታየው)
ሙሀመድ ምራቁ በረካ የሆነለት ነብይ
ሙሀመድ መላ ሰውነቱ በረካ የሆነለት ነብይ አሏሁ አክበር !!!!

እንዴት የላቀ ሙዕጂዛ ነው? ኢማሙ ሻፊዒይ እንዳሉት
«ﻣﺎ ﺃﻋﻄﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻧﺒﻴﺎ معجزة إلا وأعطى محمدا مثلها أو أكبر منها»
«አሏህ ለማንም ነብይ ሙዕጂዛን አልሰጠም ለሙሐመድ የሱን መሳይ ወይም ከዛ በላይ ከሰጠ በስተቀር»። ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም
66 viewsربنا ولا تحملنا مالا طاقة لنا به, 07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 10:38:42 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተናገሩ"አንድ ሰው በሞተ ጊዜ ዘመዶቹ በቀብር
ሥነስርአቱ ላይ ሲጨናነቁ አንድ እጅግ ያማረ ቆንጆ ሰው
በጭንቅላቱ በኩል ይቆማል።ጀናዛውም እንደተከፈነ ያ ሰው
በከፈኑ እና በሞተው ሰው ደረት መሀል ይሆናል።ከቀብር
ሥነስርአቱም በህዋላ ቀባሪ ቤተሰቦቹ ወደ ቤት ሲመለሱ ሁለት
ሙንከር እና ነኪር የተባሉ ምላኢኮች ወደ ቀብሩ በመምጣት
ጀናዛውንና ያንን ቆንጆ ሰው በመለያየት ያንን የሞተውን ሰው
በእምነቱ ጉዳይ ብቻውን በጥያቄ ሊያፋጡት ይሞክራሉ ። ሆኖም
ያ ቆንጆ ሰው ይናገራል "ይህ ሰው አጋሬም ጋደኛዬም ነው
ብቻውንም ልተወው አልችልም። እናንተ እንድትጠይቁት
ከተመደባቹ ስራችሁን መሥራት ትችላላቹ እኔ ግን ወደ ጀነት
መግባቱን ሳላረጋግጥ ትቼው እልሄድም"። ከዝያም ወደ ሞተው
አጋሩ በመዞር እንዲህ ይለዋል "እኔ አንዳንዴ ድምፅህን ከፍ
አርገህ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀስ ብለህ ስታነበኝ የነበርኩት ቁርአን
ነኝ ምንም አትጨነቅ፤ ከሙንከርና ነኪር ጥያቄና መልስ በኃላ
ምንም ጭንቀት አይኖርብህም"፤ጥያቄና መልሱም ካለቀ በኃላ ያ
ቆንጆ ሰው አል ማሉል አላ በተባሉ የጀነት መላኢኮች የተዘጋጀ
በመልካም ሽታ የሚያውድ እና ከ ሀር በተሰራ ልብስ የተዘጋጀ
አልጋ ያዘጋጅለታል።
2. ረሰል(ሶ.ዐ.ወ) እንደተናገሩት በቂያማ ቀን በአላህ ሱ.ወ ፊት
ስንቆም ከቁርአን የበለጠ ለኛ ሚከራከርልን አይኖርም
ከነብይያትም ከ መላኢኮችም በበለጠ።
3. እባክዎን ይህን መልእክት የቻሉትን ያህል ያስተላልፉ። ረሱል
(ሶ.ዐ.ወ) እውቀትን ከኔ ለሌላው አስተላልፉ አንድም አረፍተ ነገር
ብትሆን እንኩዋን ብለዋል።
4. ይህ መልእክት በ አላህ ፍቃድ በቀጣይ 7 ቀናት ቢያንስ 5
ሚልዬን ሰዎች እንዲዳረስ ዱአ እያደረግን ነው።
እባክዎን ይህን መልእክት ለ ቤተሰብዎ፣ ለዘመድዎትና
ላሚያውቅዋቸው ሁሉ በማስተላለፍ ከተትረፈረፈው የአላህ ምንዳ
ተጠቃሚ ይሁኑ።
*እርስዎ ቁርአንን ሲይዙ ሰይጣን ራሱን ያመዋል።
*ሲከፍቱት ይወድቃል።
*እያነበቡት ሲያይ ራሱን ይስታል።
*ይህንን መልእክት ሊያስተላልፉ ሲያስቡ ላማዳከምና ለማስነፍ
ይሞክራል።
እኔ አሸነፍኩት ምክንያቱም ለእርስዎ መላክ ችያለሁ።
5. እባክዎን ሸይጣንን ያሸንፉና ይህንን መልዕክት ቢያንስ ለ5
ሰው ያስተላልፉ።

https://t.me/+FrlYmPfOKbw4M2E0
69 viewsربنا ولا تحملنا مالا طاقة لنا به, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 22:50:18 :::::::::::ድንግል/ቢክራ አላገኘዉባትም:::::::

ልጅ አገረድ አገባ ግን (ቢክራ) ድንግል አላገኘባትም ??


ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ተጠየቁ :-

➪ ጥያቄ:- ሰውየው ልጅ አገረድ አግብቶ ድንግል ሁና ካላገኛት ምን ማድረግ ነው ያለበት ?

➪ መልስ:- ይሄ ብዙ ምክኒያቶች ይኖሩታል : ድንግሏ ምናልባት ያለ ዝሙት ሊፈርስ ይችላል። የልጂቱ ውጫዊ ስብዕናዋ መልካም ከሆነ እናም በዲኗ የተስተካከለች ከሆነች በሷ ላይ ጥሩ ግምትና መልካም ጥርጣሬን ማሳደር የግድ ነው። በዚያ ላይ ጥሩ ጥርጣሬን ማሳደር ግድ ይላል።

- ወይንም አፀያፊውን ዝሙት ሰርታ ከዚያ አላህ መርቷት ከሰራችሁ መጥፎ ተግባር ተፀፅታና ቶብታም ሊሆን ይችላል። ከዚያም ወደ ጥሩነትና መልካምነት ከተቀየረች (ቢክራ) ድንግል አለመኖሯ እሱን አይጐዳውም።

- ምናልባትም ድንግሏ በወር አበባ ብርታት ምከንያት ፈርሶ ሊሆን ይችላል። ጠንካራ (ሃይድ) የወር አበባ (ቢክራን)ድንግልን ያፈርሳል። ይሄህ ኡለሞች አውስተውታል።

- ልክ እንደዚሁም በአንዳንድ ዝላዮች ድንግል ሊፈርስ ይችላል። ከሆነ ቦታ ወደሆነ ቦታ ስትዘል። ወይንም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ዝቅተኛ ቦታ በምትወርድ ጊዜ በዚህ አጋጣሚ ድንግል ሊፈርስ ይችላል።

➪ ስለዚህ የድንግል መፍረስ የግድ በአፀያፊው ዝሙት ብቻ ሊሆን አይችልም። በጭራሽ። ከዝሙት ውጭ በሆነ ክስተት ነው ድንግል የፈረሰው ካለች ወይንም በዝሙት ነው ድንግሌ የፈረሰው ግን ተገድጄ እና ተደፍሬ ነው ካለች ይሄ እሱን አይጎዳውም።

- ወይንም በፍላጎቷ ዝሙት ሰርታ ከሆነ ድንግሏ የፈረሰው ግን ያንን ያደረገችው በማታውቅበትና በመሃይምነቷ ጊዜ እንደሆነም እናም አሁን ከዚያ ቶብታና ተፀፅታ ከሆነ ይሄም እሱን አይጎዳውም።

- ይሄን የሷን ሚስጥር ሊበትንባት እና ሊያሰራጭባት አይገባም ይልቁንስ ሊደብቅላት ይገባል። በእርሱ ግምት እውነተኛነቷንና ቅንነቷን እናም መስተካከሏን ካመነበት ከእርሱ ጋር ያስቀራታል። ካሎነ ግን በሷ ላይ ያደረበት ግምት ጥሩ ካልሆነ ይፈታታል የሷን ሚስጥር ከመደበቅና ከመጠበቅ ጋር በጭራሽ ሚስጥሯን ባደባባይ መግለፅ አይገባውም።

ምንጭ፡- መጅሙዕ አል-ፈታዋ 287/286-30

(ሁሴን አህመድ)


..
@Muslims_Ummahh
124 viewsربنا ولا تحملنا مالا طاقة لنا به, 19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 13:58:41 أحبب حبيبك هونا ما عسى أن يكون بغيضك يوماً ما، وابغض بغيضك هوناً ما عسى أن يكون حبيبك

“ወዳጅህን በመጠኑ ውደድ፤ ምናልባትም ወደፊት ጠላትህ ሊሆን ይችላልና። ጠላትህንም በመጠኑ ጥላ፤ የሆነ ቀን ወዳጅህ ሊሆን ይችላልና።”
(ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ)

..
@Muslims_Ummahh
139 viewsربنا ولا تحملنا مالا طاقة لنا به, edited  10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 12:52:52 اللهم...
يا مقلب القلوب ، ثبت قلبي على حبك
አላህ ሆይ !
ልብን ምትገለባብጥ የሆንከው .... ልቤን በፍቅርህ ላይ አፅናት


..
@Muslims_Ummahh
147 viewsاليوم أكملت لكم دينكم وأتممت عليكم نعمتي ورضيت لكم الإسلام دينا, edited  09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 07:59:23
የማለዳ ቁርስ
331 viewsربنا ولا تحملنا مالا طاقة لنا به, 04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 22:49:46 بسم الله الرحمن الرحيم الحمد لله رب العاملين الصلاة والسلام على ءشرف الأنبياء والمرسلين نبينا محمد صلى الله عليه وسلم السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ለዚህ ቀን ላደረሰን አላህ ምስጋና ይገባው። በመጀመሪያ እስልምና ምንድነው ከሚለው እንጀምር።
እስልምና ምንድነው???
ሸሀደቱ አንላ ኢላሀ ኢለላህ
ወሸሀደቱ አነ ሙሀመዱን ረሱሉላህ ሰ.ዐ.ወ
የኢስላም መሰረቶች 5 ናቸው።እነሡም
ሸሀደቱ አንላ ኢላሀ ኢለላህ
ወሸሀደቱ አነ ሙሀመድ ረሱሉላህ
ኢቃሙ ሰላ የ5 ወቅት
ሰላቶችን በአግባቡ መስገድ
ኢታኡል ዘካ በአመት አንዴ
ዘካ ማውጣት
ወሰውሙ ረመዳን በአመት
አንድ ወር ረመዳንን መፆም
ወሀጁል በይቲ መኒስተታዐ
ዐለይሂ ሠቢላ የአሏህን
ቤት(ካዕባ) በህይወት ዘመን
አንዴ ሀጅ ማድረግ ግዴታ ነው።
የኢማን መሰረቶች ደግሞ 6 ናቸው ።
አን ቱዕሚነ ቢላህ በአሏህ
ማመን
ወመላኢከቲሂ አሏህ በቁጥር
የማይገመቱ ብዙ መላኢኮች
እንዳሉት ማመን
ወኩቱቢሂ ብዙ ኪታቦች
እንዳሉት ማመን
ወሩሱሊሂ አሏህ ብዙ
መልዕክተኞች እንዳሉት ማመን
ከነዚህም 25 ዋና ዋናዎቹን መያዝ አለብን።
ወቢል የውሚል አኺሪ
በመጨረሻው ቀን ማመን
ወቢል ቀደሪ ኸይሪሂ ወሸሪሂ
ኩሉን ሚነሏሂ ተዓላ በፍርድ ማመን ጥሩውም
መጥፎውም ከአሏህ ነው ብሎ ማመን
ቤት ያለ ምሰሶ እንደማይቆመው እስልምና እነዚህ የእስላም እና የኢማን መሰረቶች ባይኖሩ እስልምና መቆም አይችልም ነበር ።
የዛሬው ትምህርታችን ይህን ይመስላል።
ወሠላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ።

..
@Muslims_Ummahh
177 viewsربنا ولا تحملنا مالا طاقة لنا به, edited  19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 22:13:33 የቀኑ 3ቱ ሐዲሶች
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

1) #ብልጫ አለው!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿صلاةٌ في المسجدِ الحرامِ أفضلُ من مائةِ ألفِ صلاةٍ فيما سِواهُ﴾
“በመስጂደል ሀረም የሚሰገድ ሰላት ሌላ ቦታ ከሚሰገድ ሰላት በመቶ ሺህ የሚበልጥ ብልጫ አለው።”
ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 1163

2) #ከኛ አይደለም!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿مَنْ أَفْسَدَ امرأةً على زَوْجِها فَليسَ مِنّا﴾
“ሴትን ልጅ በባሏ ላይ እንድትበላሽ ያደረገ ከኛ አይደለም።”
ምንጭ፦ ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 324

3)#ለደረቀ ልብ ፍቱን መድኃኒት!
ከአቡ ሁረይራ ( رضي ﷲ عنه) ተይዞ:  አንድ ሰው ወደ ረሱል (ﷺ) በመምጣት ቀልቡ እንደደረቀ ስሞታ አቀረበላቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉት፦
﴿إنْ أردتَ أنْ يَلينَ قلبُكَ، فأطعِمْ المسكينَ، وامسحْ رأسَ اليتيمِ﴾
“ቀልብህ እንዲለሰልስ ከፈለክ ምስኪኖችን ምግብ መግብ። የየቲሞችን (አባት የሌላቸውን ልጆች) እራስ ዳብስ።”
ምንጭ፦ ሶሂህ አልጃሚዕ: 1410



ሼር አድርጉት።
||
ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ

.. @Muslims_Ummahh
169 viewsربنا ولا تحملنا مالا طاقة لنا به, 19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 21:48:18 ☞ እናቴን ማን ነው የሚገዛኝ???? ☜

አጂብ የሆነ ታሪክ

አንድ ወጣት በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ ይወድና ለጋብቻ ያጫታል ከተጫጩ በዃላ ግን ግልፅ በሆነ አረፍተነገር እናቱን እንደማትወዳት እና አብራቸው መኖር እንደማትፈልግ ትነግረዋለች ።

እሱን ብትወደውም እናቱን ግን ልትወድለት አልቻለችም እናቱም
በእድሜ የገፉ ስለነበሩ ልጂቷ ልጂቷ ብዙ ታስቸግራቸው ጀመር።

ከዛም ልጅ እንደማያገባትና እንደሚለቃት አስረግጦ ሲነግራት ልጂቱ ልጁን ስለምትወደው ደነገጠች እንደምታስተካክልና እናቱን እንደምታከብር እንዲያገባት ተማፀነችው።

ልጁም ካስተካከልሽ ብሎ እሽ አላት ከዛም የሰርጋቸው ቀን ደረሰ ምሽቱ ላይ ሠዎች በተሰበሰቡበት መሐል እናቱ ተጋባዥ እንግዶችን ለማስተናገድ በደስታ ሽር ጉድ ሲሉ

*ሙሽሪት በንዴት ይህቼን አሮጊት እናትክን ወዳ በልልኝ አታሳየኝ ከቻልክ እንደውም ሽጣት አለችው*

ልጁም ፈገግ ብሎ ተነሳና ሰዎች ከተሰበሰቡት መሐል
*"እናቴን ማን ነው የሚገዛኝ "ለ 3 ጊዜ በተከታታይ ማለት ጀመረ*

እናቱም ከልጃቸው አንደበት የሰሙትን ማመን አቃታቸው ማዘንና ማልቀስ ጀመሩ እንግዶቹን በጣም ተገረሙ አዘኑ ከዛም ሙሽራው ወደ ሙሽሪት ዘወር አለና
*"አየሽ እናቴን ማነም ሊገዛት አልቻለም
ለምን እንደሆነ ታቂያለሽ? ምክንያቱም እናት ውድ ነች እናቴ ከምንም በላይ ውድ ነች ዋጋ አይተምናትም እኔ ግን
እናቴን እገዛታለው አንችን ደግሞ ሺጨሻለው

* ፈትቸሻለው በማለት የሰርጉ ቀን ቀለበቱን ከፊቷ ላይ በመወርወር ትቶላት" እናቱን ይዞ ሲወጣ ወዲያው ከእንግዶቹ አንዱ ተከተለውና እንዲክ አለው "

*ለሴት ለልጄ ከአንተ የተሻለ ጥሩ ልጅ
አላገኝም ፍቃደኛ ከሆንክ ልጄን ልዳርልክ*
ብሎት ልጁን ይዞ ወደ ቤቱ ወሰደው ልጁም የዛን ሰው ልጅ ሲመለከታት እጅግ ውብና አደበኛ ነበረች አገባትም ለባሏም ሆነ ለባሏ እናት ፍቅሯን ያለ ገደብ ትሰጣቸውና ትንከባከባቸው ጀመር።

የወለደቻት እናቷ እስክትመስላት ድረስ
የሚጠበቅባትን ሁሉ መወጣት ጀመረች።

መልካምና ደስተኛ የሆነ ህይወት ይኖሩ ጀመር።

*አንድን ነገር ለ አሏህ ብሎ የተወ አሏህ የተሻለውን ይወፍቀዋል*

እህቴ ከታሪኩ ብዙ ቁምነገሮችን ተማሪበት፣ ለጓደኞችሽም አጋሪው

➦ምርጥ ትምህርት ያገኛሉ ቨ
የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ

..
@Muslims_Ummahh
186 viewsاليوم أكملت لكم دينكم وأتممت عليكم نعمتي ورضيت لكم الإسلام دينا, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 17:31:58 መልካም ባህሪያት


"አቡ ደርዳዕ (ረዲየላሁ አንሁ) ነብዩ እንዲህ ብለዋል ‹‹በዕለተ ቂያማ ከአማኝ የመልካም ስራዎች ሚዛን ውስጥ ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የሚከብድ ስራ የለም፡፡ አላህ ባለጌን አይወድም፡፡"

ሐዲሱን ቲርሚዚይ ዘግበውታል

‹‹ እምነትን መሰረት ያደረገ መልካም ስነ ምግባር በዕለተ ቂያማ ሚዛን ይደፋል፡፡
‹‹ አላህን ባለጌን አይወደውም በሁለቱም አለማት ከሳሪ ነዉ።

.. @Muslims_Ummahh
199 viewsربنا ولا تحملنا مالا طاقة لنا به, 14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ