Get Mystery Box with random crypto!

ከ3000 በላይ የሙዕጂዛ_ባለቤት °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° | Muslims Ummah 🌍

ከ3000 በላይ የሙዕጂዛ_ባለቤት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ሙሀመድ ጨረቃ ለሁለት የተከፈለለት ነብይ
ሙሀመድ ከጣቶቹ መሃል ውሃ የፈለቀለት ነብይ
ሙሀመድ የታላቁ ሙዕጂዛ የቁርአን ባለቤት የሆነ ነብይ
ሙሀመድ ወደሱ ግመል እያለቀሰ በመምጣት የበደል ስሞታ ያቀረበለት ነብይ
ሙሀመድ ደረቅ እንጨት በሱ ናፍቆት ያለቀሰለት ነብይ
ሙሀመድ ተኩላ የአላህ መልዕክተኛ መሆኑን የመሰከረለት ነብይ
ሙሀመድ ዛፍ መሬት እየቀደደች ወደሱ በመምጣት መልዕክተኝነቱን የመሰከረችለት ነበይ
ሙሀመድ በጦርነት ምክንያት የወጣችን የቀታዳን አይን ወደቦታው የመለሰለት ነበይ
ሙሀመድ የታላቁ ምልጃ ባለቤት የሆነ ነብይ
ሙሀመድ የቀብር ሰዎች ዋይታ ይሰማው የነበረ ነበይ
ሙሀመድ የኢስራእና የሚዕራጅ ባለቤት የሆነ ነብይ
ሙሀመድ ሁሉንም አንቢያዎች በበይተል መቅዲስ ኢማም ሆኖ ያሰገደ ነብይ
ሙሀመድ ጀነትና ጀሃነምን በአይኑ ያየ ነብይ
ሙሀመድ የኡሁድ ተራራ የተንቀጠቀጠለት በኋላም "ተረጋጋ" ብለው እግሩን ሲያሳርፍበት የተረጋጋለት ነብይ
ሙሀመድ ምግብ በእጃቸው ላይ ሆኖ ተስቢህ የሚያደርግለት ነብይ
ሙሀመድ ድንጋዩም ዛፉም ሰላምታ የሚያቀርብለት ነበይ
ሙሀመድ እሳቸውን በመግደል ሴራ የተመረዘው ስጋ እንዳይበሉት የተመረዘ መሆኑን በመናገር ራሱን ያጋለጠለት ነበይ
ሙሀመድ ለእርድ የቀረቡ ስድስት ግመሎች ቅድሚያ በሱ እጅ ለመታረድ የተሽቀዳደሙለት ነብይ
ሙሀመድ አይነስውር ሰውየ በነገሩት የተወሱል ዱዓ አይኑን ያበራለት ነብይ
ሙሀመድ በበድር ዘመቻ ጊዜ ከውጊያ በፊት የእያንዳንዱን ሙሽሪክ መውደቂያ(መገደያ) ቦታ " እገሌ እዚህ ቦታ ይወድቃል እገሌ እዚህ ቦታ ይገደላል" በማለት ቀድሞ የተናገረ በኋላም ሳይዛነፍ እንዳለው የሆነለት ነብይ
ሙሀመድ ከፊቱ እንደሚያየው ከኋላውም የሚያይ ነብይ
ሙሀመድ ላቡ ከሚስክ የበለጠ መአዛ የነበረው ነብይ
ሙሀመድ ለዛቱ ጥላ የሌለው ነብይ
ሙሀመድ ትንሽ መጠጥና ምግብ በሱ በረካ እጅግ በርካታ ሰውና ሰራዊት ያጠግብለት የነበረ ነብይ
ሙሀመድ ድምፁ ማንም ሊያደርስበት በማይችልበት ቦታ ላይ የሚደርስለት ነብይ
ሙሀመድ በዘመቻ ላይ የመላኢካ ወታደሮች ኑስራ(እርዳታ) የሚያደርግለት ነብይ
ሙሀመድ የሱ ዳበሳ በረከት የሆነለት ነብይ (ለምሳሌ በሀንዞላ እንደታየው)
ሙሀመድ ምራቁ በረካ የሆነለት ነብይ
ሙሀመድ መላ ሰውነቱ በረካ የሆነለት ነብይ አሏሁ አክበር !!!!

እንዴት የላቀ ሙዕጂዛ ነው? ኢማሙ ሻፊዒይ እንዳሉት
«ﻣﺎ ﺃﻋﻄﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻧﺒﻴﺎ معجزة إلا وأعطى محمدا مثلها أو أكبر منها»
«አሏህ ለማንም ነብይ ሙዕጂዛን አልሰጠም ለሙሐመድ የሱን መሳይ ወይም ከዛ በላይ ከሰጠ በስተቀር»። ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም