Get Mystery Box with random crypto!

ሚሊንየም አደራሸ አካባቢ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሁለት ሰዎች ተገደሉ። የአዲስ አበባ ፖሊስ መግ | Muktarovich Ousmanova

ሚሊንየም አደራሸ አካባቢ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሁለት ሰዎች ተገደሉ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ መግለጫ የሚከተለው ነው
"
የጽንፈኛው ቡድን አባላት የሆኑት ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ የተባሉት የጽንፈኛው ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተልዕኮ ይዘው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የጸጥታ አካላት ባደረጉ ክትትል ደርሰዉበት የሽብር ተግባራቸውን ሳይፈፅሙ በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ጽንፈኞቸ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆናቸዉ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ አይሱዙ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም ከፖሊስ አባላት ጋር በተደረገ የተኩስ ልዉዉጥ የጽንፈኛው ቡድን መሪ ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ሲሞት ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል ተገድሏል፡፡
አቤኔዘር ጋሻው አባት የተባለው የቡድኑ አባል ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ጽንፈኞቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ ሲቆስሉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ ፅንፈኞቹ በመኪናቸው እንዲጭኗቸው ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በፅንፈኛው አባላት ተገድለዋል፡፡

አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል ፡፡ በቀጣይ ፖሊስ የደረሰበትን ዝርዝር መረጃ እንደሚገልፅ አስታውቋል፡፡
Addis Ababa Police "