Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋች ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የጅምላ ግድያ መበራከት አሳ | Muktarovich Ousmanova

ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋች ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የጅምላ ግድያ መበራከት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል አለ።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጥር ወር በአማራ ክልል መራዊ ከተማ የተፈጸመ “የጅምላ ግድያን” አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የመንግስት ቸልተኛነት ለከፋ ጉዳት አጋላጭ ሆኗል በማለት ወቅሷል።

በአማራ ክልል ጥር 21 ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በነበረበት ዕለት ከ50 የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸውን መረጃ አግኝቻለሁ ያለው የመብት ድርጅቱ፤ ከ20 የሚበልጡ አስክሬኖች በመንገድ ላይ ተጥለው የሚያሳይ የሳተላይት ምስል ዛሬ አጋርቷል።

“የኢትዮጵያ መንግስት ተአማኒነት ያለው ጥረት አለማድረጉ የተገደሉት ቤተሰቦች ፍትህ እንዳያገኙ፣ መሰል ወንጀሎች ለመከላከል እንዳይቻልና ለከፋ ጉዳት የሚያጋልጥ ሆኗል” ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል መንግስትን ወቅሷል።

ከሦስት ሳምንታት በፊት የመራዊ ጥቃትን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶችን ለኢትዮጵያ መንግስት መላኩን ያስታወቀው ድርጅቱ፤ እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ እና እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጿል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በግድያው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ለፋኖ የሚዋጉ ሰዎችን ቤት ለቤት በመፈለግ እንደወሰዱ እና አንዳንዶችን ደግሞ ያሉበትን እንዲጠቁሙ በማስገደድ ከቤት እየወሰዱ እንደገደሉ አመልክቷል።

ከአንድ ዓመት በፊት የመንግስታቱ ድርጅት መርማሪዎች ይፋ እንዳደረጉት ከሆነ ለሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ በቆየው ትግራይ ክልል ብቻ ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ ከ48 በላይ “ትላልቅ” ግድያዎች ተፈጽመዋል።

ይኹን እንጂ ጥር 24 ቀን 2016 ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዙ ወንጀሎች በተመለከተ የፌደራል መንስግቱ “ተገቢውን እርምጃ በእርሱ በኩል” መውሰዱን እንዳስታወቀ አዲስ ማለዳ ዘግባ ነበር።