Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች እንደአዲስ ሊዋቀሩ ነው ተባለ በቅርብ ጊዜያት | Muktarovich Ousmanova

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች እንደአዲስ ሊዋቀሩ ነው ተባለ

በቅርብ ጊዜያት በርካታ ቅሬታዎችን ያስተናገደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉምሩክ የስራ ክፍል፤ ሰራተኞች በአዲስ መልክ እንደሚደራጁ የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

ከብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በ2016 ስምንት ወራት ውስጥ 49 የጉምሩክ ሰራተኞች እና ከፍተኛ አመራሮች ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

ኮሚሽኑ በሰራተኞቹ ላይ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለመቅረፍ "ረጅም ጊዜ" የወሰደ ጥናት መካሄዱ ታውቋል።

በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰሩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞን ለመቀየር፣ ለማሸጋሸግ እና በድጋሚ ለማዋቀር ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል።

በመጋቢት መጀመሪያ "በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ አሉባልታዎችና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ከእውነት የራቁ ናቸው" በማለት የብሔራዊ የአየር ትራንስፖርት ፋሲሊቲ ኮሚቴ መግለጫ ቢሰጥም አየር መንገዱ በበኩሉ በቅሬታዎቹ ላይ ምርመራ መጀመሩን እንዳስታወቀ ከዚህ ቀደም የመረጃ ምንጫችን መዘገቡ ይታወሳል ።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ