Get Mystery Box with random crypto!

ላይመለስ ሄዷል | #ነፍስ_ኄር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባህርዳር ከተማ አማካይ | Muktarovich Ousmanova

ላይመለስ ሄዷል | #ነፍስ_ኄር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባህርዳር ከተማ አማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት ተሰምቷል ።

ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ፤ ለሀዋሳ ከተማና ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎቱን ሰጥቷል ።

በቅርቡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስርአተ-ጋብቻዉን የፈፀመው ተጨዋቹ በጉዳት ምክንያት ከክለቡ ስብስብ ጋር ያልነበረ ሲሆን በትዉልድ ቦታው አርባምንጭ መጋቢት 18/2016 ዓ.ም ንጋት ላይ ህልፈተ ህይወቱ ተሰምቷል ።

የቀብር ስነስርዓቱም በዛሬው ዕለት በአርባ ምንጭ ከተማ እንደሚፈፀም ታዉቋል ። ለቤተሰቦቹ ፣ ለቡድን አጋሮቹ ፣ ለአድናቂዎቹ እንዲሁም ለመላው የስፖርት አፍቃሪ መፅናናቱን ይስጥልን ።

[ አሟሟቱን በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ሲሆን '' #ራሱን_አጠፋ '' የሚለዉ ከሚወጡት መረጃዎች አንዱ እና ዋነኛው ነው ]