Get Mystery Box with random crypto!

ከሚደርሱኝ ጥቆማዎች በመነሳት ማረጋገጥ የቻልኳቸው የቤት ፈረሳ መረጃዎች - አያት ዞን አንድ ው | Muktarovich Ousmanova

ከሚደርሱኝ ጥቆማዎች በመነሳት ማረጋገጥ የቻልኳቸው የቤት ፈረሳ መረጃዎች

- አያት ዞን አንድ ውስጥ ያሉ በርካታ 'ዘመናዊ' ሊባሉ የሚችሉ መኖርያ ቤቶች ስፍራው ለሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ግንባታ ስለሚፈለግ ተነሱ እንደተባሉ፣ ባለፈው እሁድ እለት በመንግስት አካላት ስብሰባ ተጠርተው ይህ በይፋ እንደተነገራቸው አረጋግጫለሁ። ይህ በአካባቢው ቤቶችን የማንሳት ጉዳይ ቀጣይ እንደሆነም ታውቋል።

- በቦሌ ክ/ከተማ በተለምዶ ጉርድ ሾላ ንግድ ባንክ አካባቢ አስፓልት ዳር ያሉ የግል ቤቶች ተለክተው አንዳንዱ ቤት እስከ ሳሎኑ፣ አንዳንዱ ደግሞ እስከ መኝታ ቤት ድረስ እንዲፈርስ መደረጉ ታውቋል። እስከ ሳሎን ድረስ ብቻ በልኬት የፈረሰባቸው ቀሪውን መኝታ ቤታቸውንና ኪችናቸውን ዛሬ ለመሸፈን መግቢያና መውጪያ በራቸውን ሲሰሩ በድጋሜ አፍርሰውባቸው እንደገና ፍቃድ አውጡ እንደተባሉ ተረጋግጧል።

#AddisAbaba

Photo: File
ኤሊያስ መሰረት ያጋራው