Get Mystery Box with random crypto!

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ያቋቋመው መርማሪ ኮሚሽን፤ የኢትዮጵያ መንግስትን ወቀሰ በ | Muktarovich Ousmanova

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ያቋቋመው መርማሪ ኮሚሽን፤ የኢትዮጵያ መንግስትን ወቀሰ

በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመመርመር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ያቋቋመው ኮሚሽን፤ የመርማሪ ቡድን ወደ ሀገሪቱ ለመላክ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም “የኢትዮጵያ መንግስት አልፈቀደልኝም” ሲል ወቀሳ አቀረበ። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ፤ ኮሚሽኑ “በተቀመጠለት ኃላፊነት መሰረት ገንቢ በሆነ መልኩ አብሮ ለመስራት ዝግጁ አልነበረም” ሲል ተችቷል።

የመርማሪ ኮሚሽኑ ወቀሳ እና የኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ የተደመጠው፤ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ነው። ባለፈው የካቲት ወር አጋማሽ የተጀመረው እና እስከ መጋቢት 26፤ 2015 በሚዘልቀው በዚሁ ዓመታዊ ጉባኤ፤ የበርካታ ሀገራት የሰብዓዊ መብት ይዞታን የተመለከቱ ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

ትላንት ማክሰኞ መጋቢት 12፤ 2015 በነበረው የምክር ቤቱ ውሎ፤ የኢትዮጵያ እና ቬንዙዌላን ወቅታዊ ሁኔታ የተመለከቱ ማብራሪያዎች ቀርበዋል። ኢትዮጵያን የተመለከተውን ማብራሪያ ለምክር ቤቱ በንባብ ያሰሙት፤ ሶስት አባላት ያሉትን መርማሪ ኮሚሽን በሊቀመንበርነት የሚመሩት ታንዛኒያዊው መሐመድ ቻንዴ ኦትማን ናቸው።

መርማሪ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባቀረበው ሪፖርት፤ በኢትዮጵያ በጥቅምት 2013 ውጊያ ከተቀሰቀሰ በኋላ በግጭቱ የተሳተፉ ሁሉም ወገኖች የጦር ወንጀሎች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ አሳማኝ ምክንያቶችን ማግኘቱን ሊቀመንበሩ በማብራሪያቸው አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያን ኢንሳይደር

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ:- https://ethiopiainsider.com/2023/10175/