Get Mystery Box with random crypto!

የጅማ ሀገረ ስብከት ተሽከርካሪዎቹን እንዳያንቀሳቅስ ታገደ። የጸጥታ ኀይሉ ዋና ሥራ አስኪያጁን ከ | Muktarovich Ousmanova

የጅማ ሀገረ ስብከት ተሽከርካሪዎቹን እንዳያንቀሳቅስ ታገደ።

የጸጥታ ኀይሉ ዋና ሥራ አስኪያጁን ከወሰዳቸው በኋላ፣ የሀገረ ስብከቱ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ መኾኑን፣ ከበላይ አካል የተሰጠ ነው ያለውን ትእዛዝ በመጥቀስ አስታውቋቸዋል፤ ተብሏል።

የዋና ሥራ አስኪያጁም መኖሪያ ቤት በጸጥታ አካሉ ቪዲዮ እየተቀረጸ ፍተሻ እንደተካሔደበት ተገልጿል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ ዛሬ ማለዳ መኖሪያ ቤታቸው ተፈትሾ ከመወሰዳቸው አስቀድሞ፣ በዛሬው ዕለት በሚከበረው የቅዱስ ዑራኤል በዓል ላይ ለመገኘት፣ ወደ ደብረ በረከት ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ለማምራት እየተዘጋጁ የነበረ ሲኾን፣ በአሁኑ ወቅት ከተወሰዱበት ተመልሰው በደብሩ እንደሚገኙ ታውቋል።"