Get Mystery Box with random crypto!

ጠቃሚ ኢንፎርሜሽን ለኢትዮጵያዊያን ~~~ //~~~ ላለፉት ጥቂት የማይባሉ ዓመታት ካሊፎርኒያን | Muktarovich Ousmanova

ጠቃሚ ኢንፎርሜሽን ለኢትዮጵያዊያን
~~~ //~~~
ላለፉት ጥቂት የማይባሉ ዓመታት ካሊፎርኒያን የዝናብ ጠብሽ ወግሯት እንደነበር ይታወሳል :: ዘንድሮ ግን በመላው ካሊፎርኒያ በንፅፅር ሲታይ ከበቂ በላይ የሚባል ዝናብ ዘንቧል :: የካሊፎርኒያ የውሃ ሪዘርቬሽን ቋቶችም ከ 45 እስከ 50 ፕርሰንት ሞልተዋል ተብሏል ::
በተለይ ከዚህ ወር መግቢያ ጀምሮ በጣለው ተከታታይ ከባድ ዝናብ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ደርሷል :: በተለይም በርካታ የስቴቱ የፍጥነት ማሽከርከሪያ መንገዶች (highway) በዝናብ የመቦርቦር ጉዳት (pothole) ደርሶባቸዋል ::በመሆኑም የካሊፎርኒያ መንገዶች ባለስልጣን ( CALTRANS) የተጎዱ መንገዶችን በፍጥነት ጠግኖ ለአገልግሎት ማብቃት የኔ ኃላፊነት ነው :: ይህ ሳይሆን ቀርቶ ሰዎች በተጎዱ መንገዶች ላይ ሲያሽከረክሩ መኪናቸው የተሰበረባቸውን ወይም የአካል ጉዳት ያጋጠማቸውን ሰዎች የጥገና ወጪ እስከ 10,000 ዶላር ድረስ እኔ ነኝ የምሸፍነው ብሏል :: ስለዚህ በዚህ አይነት ሁኔታ የመኪናችሁ መካኒካል ፖርት የተሰበረባችሁ ኢትዮጵያዊያን ካላችሁ : ኢቭን መኪናችሁ ሲንገጫገጭ የአካል ጉዳት ደርሶባችሁ ከሆነ ወደ caltrans ዌብሳይት በመሄድና ለጥገና ወይም ለህክምና ያወጣችሁትን ደረሰኝ አያይዛችሁ በመላክ ያወጣችሁትን ወጪ ማስመለስ ትችላላችሁ ::
አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዬ ጊዜ መንግስት በቆፈረው ጉድጏድ ውስጥ ወድቃችሁ የተጎዳችሁ ወገኖቼ ደግሞ ''እያያችሁ አትሄዱም ወይ''ተብላችኃል::

If you sustained pothole damage to your car on the freeway or any other California highway, you'll want to file your claim with Caltrans. Caltrans will reimburse up to $10,000 or less for damages or injuries caused by a pothole, and it doesn't require a filing fee.
ኑረዲን ኢሳ