Get Mystery Box with random crypto!

መከላከያ ሰራዊት ዓዲግራት ከተማ በመግባት ከጦርነቱ በፊት ይጠቀምበት በነበረው ወታደራዊ ካምፕ መቀ | Muktarovich Ousmanova

መከላከያ ሰራዊት ዓዲግራት ከተማ በመግባት ከጦርነቱ በፊት ይጠቀምበት በነበረው ወታደራዊ ካምፕ መቀመጡ ተገለጸ
=======#=======

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ማክሰኞ ጥር 9/2015 ዓዲግራት ከተማ መግባቱን እና ከጦርነቱ በፊት ይጠቀምበት የነበረው ወታደራዊ ካምፕ መቀመጡን የከተማዋ ከንቲባ ላዕከ ተስፋ ገለጹ።

“በሥምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ አዲግራት ገብተዋል” ያሉት ላዕከ “የከተማው አስተዳደርም በቦታው ነው ያለው። ፖሊስና የሚሊሺያ አካላትም በሕገ መንግሥቱ መሰረት ሥራቸውን እያከናወኑ ነው” ማለታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

የኤርትራ ሰራዊት አባላት በከተማዋ ቅርብ ርቀት ላይ እንደሚገኙ የገለጹት ከንቲባው፤ የሰራዊቱ አለመውጣት ኅብረተሰቡ ላይ ሥጋት መፍጠሩንም ጨምረው ተናግረዋል።

ቪኦኤ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘው በሰልፍ በሰላም ሲገቡ ማየታቸውንና በዚህም ምንም ስጋት እንደሌለባቸው ገልጸው፤ ነገር ግን የኤርትራ ሰራዊት በከተማዋ ቅርብ ርቀት ላይ መኖሩ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል።

የኤርትራ መንግሥት በተደጋጋሚ እየተወነጀለ በሚገኝበት ከትግራይ ክልል ሙሉ ለሙሉ ለቆ የመውጣት ጉዳይ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

በሌላ በኩል ለኹለት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ተሳታፊ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች ከሽረ እና ከአክሱም ለቀው ወደ ድንበር አቅጣጫ በመሄድ ላይ ናቸው ሲል ሮይተርስ የዓይን እማኞቹን ጠቅሶ ከሳምንት በፊት መዘገቡ ይታወሳል።