Get Mystery Box with random crypto!

ደጀኑ ወልዲያ ስለ ወልዲያ ሕዝብ ደግነትና ደጀንነት በኩራት እንድናገር ከሚያደርጉኝ ምክንያቶች አ | Muktarovich Ousmanova

ደጀኑ ወልዲያ

ስለ ወልዲያ ሕዝብ ደግነትና ደጀንነት በኩራት እንድናገር ከሚያደርጉኝ ምክንያቶች አንዱ በጋሸና ግንባር ተሰልፎ የነበረ ወታደርን በተመለከተ የሰማሁት ታሪክ ነው። ያኔ ወልዲያ በጨለማ ውስጥ በነበረበችበት ጊዜ ወታደሩ ሁሉ ቀን ከሌት ያንን ደግና ጀግና ሕዝብ ለመታደግ ዕድል የሚያገኝበትን ቀን ይመኝ ነበር። የወልዲያን ሕዝብ እንግዳ ተቀባይነት የቀመሰው ሁሉም ወታደር "መቼ ነው ወልዲያን ነጻ እንድናወጣ ትዕዛዝ የሚሰጥን" እያለ ይጠይቅ ነበር። በሌላ ግንባር ያለው ሃይል ወደ ወልዲያ ሲቃረብ ከተማዋን ነጻ የማውጣት ዕድል ባለማግኘቱ የሚ'ቆጨው ወታደር ብዙ ነበር። ለወልዲያ ሕዝብ ብንሞትለት ያንሰዋል፣ ዘር ሳይለይ ሁሉንም ልጁ አድርጎ ተንከባክቦናል ይላሉ። በእርግጥ መከላከያው ወደ ወልዲያ ተመልሶ ሲገባ ቃለ-ምልልስ የተደረገለት ሰው እንባ እየተናነቀው ምንም የለን በባዶ እጅ እንዴት እንቀባላችሁ ብሎ የተናገረበት ድምጸት የነገሩን ሃቅነት የሚያረጋግጥ ነው።

ምን ለማለት ነው?

እርግጥ ነው። ኑሮ ተወዷል። እርግጥ ነው። ብዙ ሰው የሚያስተባብረው መሪ አጥቶ ተቸግሯል። እርግጥ ነው። ያልተጠበቀው የወያኔ ወረራ በርካታ ሰዎችን አስደናግጧል። ይሁንና ከመላው ኢትዮጵያ ተሰባስቦ በወሎ - ራያና የጁ ምድር አዲስ ታሪክ እየጻፈ ያለውን የሀገር መከላከያውን ልዩ ሃይላችንና ፋኖውን መደገፍ ያስፈልጋል። አሁን በሉ ተጠራሩና ያስለመዳችሁትን አድርጉ!
ወገን ተጠራራ! ደጀን ሁን!!
Woldia Times