Get Mystery Box with random crypto!

ዝምብለህ መልካም ዝራ ይበቅላል። የዘራህበት ቦታ ቢጠፋህ እንኳ አንድ ቀን ፍሬው ከፍ ብሎ እዚህ እ | ABX

ዝምብለህ መልካም ዝራ ይበቅላል። የዘራህበት ቦታ ቢጠፋህ እንኳ አንድ ቀን ፍሬው ከፍ ብሎ እዚህ እኮ ነው የዘራኸኝ ይልሃል። ስለሆነም ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ለፍጡራን ሁሉ መልካምን ዝራ። ዉጤቱን አየህ አላየህ፣ ተጠቀምክ አልተጠቀምክ ዝራ። የት፣ መቼ እና እንዴት እንደማታገኘው ባታውቅም ዝራ።
መልካም ነገር መብቀሉም ለሌሎች መትረፉም አይቀርም። ዛሬ በዱንያ ይሁን ነገ በአኺራ ምርጥ ዉጤቱን ታገኛለህ። ሰዉን ለማስደስት ኑር ትደስታለህ። ስጥም ታገኛለህ። የማንንም ደስታ አትስረቅ፣ የማንንም ቀልብ አትስበር። ዕድሜያችን አጭር ነው ወዳጆቼ። መልካም አሻራ ግን ቀሪ ነው።

ሰባሐል ኸይር!

http://t.me/MuhammedSeidABX