Get Mystery Box with random crypto!

የሰርጓ ለታ (2) ... አዎን ነበረች ... ጉዳዩን ሲጨርስ፣ ባደረገው ረክቶም ግራ ተጋብቶም ዞ | ABX

የሰርጓ ለታ (2)
...
አዎን ነበረች ...

ጉዳዩን ሲጨርስ፣ ባደረገው ረክቶም ግራ ተጋብቶም ዞሮ ተኛ፣ ….
እሷ ግን የባሰዉኑ ደከመች፣ ተዝለፈለፈች፣ ራሷን ሳተች፡፡
ድንገት ዞር ብሎ አዳመጣት፣ ትንፋሷን ሲያጣ ደነገጠ፣ ቶሎ ለባበሰና ታክሲ ጠርቶ ወደ አንድ ሆስፒታል ወሰዳት፣ የተለያዩ ድጋፎች ከተደረጉላት በኋላ ጠዋት አካባቢ ነቃች፡፡

ልክ ስትነቃ አንዲት ሐኪም ፊትለፊቷ ቁጭ ብላለች፡፡ ምን እንደሆነች፣ የት እንዳለች ለማወቅ ሞከረች። ሓኪሟ አረጋጋቻት፣ ጠየቃቻትም፡፡ ሙሽራ ስለመሆኗ እና ከትናንት ጀምሮ የሆነዉን ሁሉ አንድ በአንድ ነገረቻት፡፡

ሰዉነቷን፣ ኃፍረተ ገላዋንና ማህፀኗን ሁሉ ገልጣ በደንብ አየቻት፣ ፈተሸች፡፡ ባየችው ነገር በጣም ደነገጠች፣ ብዙ ደም ፈሷታል፣ በጠላት የተደረገ በሚመስል መልኩ ማህፀኗ ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ ሐኪሟ በርግጥ እንዲህ ያደረጋት የገዛ ባሏ ስለመሆኑ ተጠራጠረች፣ ባሏን አስጠርታ የቻለችዉን ያህል ተቆጣችው፡፡ ፀፀት ገባው። ያለመታገስ ያመጣበት ጣጣ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ተረዳ።
የተጎዳ አካሏን ተሰፋች፤ ሥነልቦናዊ ህክምናም ተደረገላት። ከ15 ቀን በኋላ ነበር ከሆስፒታል እንድትወጣ የታዘዘችው፡፡
በዚህን ጊዜ ግን ወደ ቤቱ አልገባም ብላ አስቸገረች፡፡ ሰዉዬው አውሬ እንጂ ሰው መስሎ አልታይ አላት። ቤቱም የዱር አውሬ ቤት መሠላት። ቤተሰብ ስለጉዳዩ የሚያውቀው ነገር ስላልነበር በልጃቸው ድንገተኛ የባህሪ መቀያየር ሁኔታና በዉሳኔዋ ግራ ተጋባ፡፡
ኋላ ላይ በሱ ከባድ ፀፀት፣ ለቅሶ እና በቤተሰብ ብዙ ልመና ወደ ቤቱ ሄደች፡፡ ግና ቤቱ ምቾት ነሳት። እያንዳንዱ ቀን የዓመት ያህል ረዘመባት፤ በቀረባት ቁጥር ጥፍርና ጥርስ አውጥቶ የሚመጣባት የዱር አውሬ እንጂ ሰው መስሎ አይታያትም፡፡ በተለይ ምሽት በመጣ ቁጥር እንደ ህፃን ልጅ ትባንናለች፣ ትደነግጣለች፣ ትፈራለች፣ ትጨነቃለች፡፡ እንዲሁ በስጋት እንደተናጠች ሦስት ወራትን አብራው አሳለፈች፡፡ ለሱም ለሷም ጥሩ ጊዜ አልነበረም ።

ሁኔታው እየከፋ ሲሄድ ፍች ጠየቀች። እሱ ፈቃደኛ አልነበረም። በመጨረሻም ከብዙ ጭቅጭቅና ልመና በኋላ ተፋታች።

ቀናት አልቆሙም ፣ የአላህ ነገር ሆነና በመጀመርያው ቀን ክስተት ብቻ አርግዛ ነበር፡፡ ቀናት በገፉ ቁጥር ሆዷም ገፋ፣ ዘጠኝ ወር ሞላ፣ ምጥ ሲመጣ ሆስፒታል ገባች፡፡
ሊያዩዋት ወደ ማረፊያ ክፍል ወስደው አስተኟት። አልጋዋ ላይ እንዳደረጓት በዐይኖቿ ጠርዞች ክብልል እያለ የሚወርደዉን እንባዋን መገደብ ተሳናት፡፡ ሌላ ስጋት ገባት፣ ሌላ መሸማቀቅ አሳሰባት። ተከታታዩዋ ነርስ ተደናግጣ ምን እንደሆነች ጠየቀቻት፡፡

ታሪኳን እንደደገና እንደ አዲስ አወራች፣ ፍርሃቷንም ገለፀች፡፡ በዚያን ቀንም ቤተሰቦቼ ሚስጢሯን ሁሉ ሰሙ፡፡ በሰሙት ነገር ተቆጩ፣ ተበሳጩ፣ አዘኑ፣ ተቆጡ፣ እስከዛሬ ያን ሁሉ ስቃይሽን ለምን ደበቅሽን አሉ። በርግጥ ልጃቸው ጉዳት ላይ ነበር የከረመችው።
 በመጨረሻ ልጅ ተወለደ፡፡  በኦፕራሲዮን ነበር የወለደችው፡፡  
.....

ይቀጥላል



http://t.me/MuhammedSeidABX