Get Mystery Box with random crypto!

ሙሀመድ ሰዒድ Mohammed seid

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedsei — ሙሀመድ ሰዒድ Mohammed seid
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedsei — ሙሀመድ ሰዒድ Mohammed seid
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedsei
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 924
የሰርጥ መግለጫ

https://t.me/muhammedsei

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-11 22:48:06 ብልጥና አዋቂ ስለሆንኩ ኢስላምን አልያዝኩም፤
ሞኝና መሃይም ስለሆንኩም አልጠመምኩም።
.
ቅናቻ ከአላህ ነው
እሱ የሻውን ያጠማል
ለሻም ሰው ቅናቻን ይሠጣል።

ያ ረብ

ከሠጠኸን በኋላ አትንሳን
ከመራኸን በኋላ አታንሸራተን
ካስገባኸን በኋላ ከዲንህ አታስወጣን።

http://t.me/MuhammedSeidABX
180 viewsMohammed Seid, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 14:45:20 ዑመር ተፅዕኖ ፈጣሪው ፊልም በአማርኛ
*
ውድና የተከበራችሁ የአል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ወዳጅና ተከታታዮች ባለፉት ቀናት በአንጋፋውና እውቁ የዐረበኛ ፊልሞች ዳይሬክተር ሐቲም ዓሊ የተሰራውንና ከተለያዩ የዐረብ ሀገራት ብቁ የሆኑ ተዋናዮች ተጣምረው የተወኑበትን ዑመር የተሰኘ ፊልም በትርጉም ይዘንላችሁ እንደምንመጣ አሳውቀን ነበር።

እነሆ ይህን የቅርብ ጊዜና መላው ዓለም ላይ ተፅዕኖ የፈጠረ ጉደኛ ተከታታይ ፊልም በባለ ሁለንተናዊ ሙያና ክህሎቱ የጥበብ ሰው ሷሊሕ አስታጥቄ በላቀ ብቃት ወደ አማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ፣ በተለያዩ ማዲሆችና ተዋናዮች ድምፅ አቻ ለአቻ ተተውኖ ፣ በአል ፋሩቅ አዲስ ስቱዲዮ ውስጥ በተዋጣለት የኤዲቲንግ ባለሙያው ዐብዱለጢፍ ዐሊ (አንበስ) ኤዲት ተደርጎ ፣ በከፍተኛ ጥራት በ30 ክፍል ወደናንተ ሊደርስ ቀናት እየጠበቀ ይገኛል።

መልቲሚዲያችንም አሁን ከሚሰራበት የመንዙማ ስራዎች ጎን ለጎን የቀደመውን የፊልም ትርጉም ስራ ዳግም መጀመሩንና ከዚህ በኋላም በርካታ ፊልሞችን ወደናንተ ለማድረስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

ይህ ከትርጉም ጀምሮ እስከ ትወና እንዲሁም እስከ ኤዲቲንግ ድረስ በርካታ ብቁ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ፊልም በቅርብ ቀን በዩቲውብ በቴሌግራም ቻናሎቻችን ይለቀቃሉ። ከእናንተ የሚጠበቀው ዩቲዉብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ፣ የቴሌግራም ቻናላችንን ደግሞ ጆይን አድርጎ መጠበቅ ብቻ ነው።

የዩቲውብ ገጻችን Youtube:

https://youtube.com/c/ALFARUKISLAMICTUBE

የቴሌግራም ገፃችን Telegram

https://t.me/ethioalfaruk

የፌስቡክ ገፃችን Facebook

https://www.facebook.com/alfarukmultimediaproduction/
-------------------

Share Share Share
210 viewsMohammed Seid, 11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 14:45:15
190 viewsMohammed Seid, 11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 18:24:58 ጌታዬ ሆይ የአቅሜን ውስንነት እና የብልሃቴን እጥረት ወዳንተው አቤት እላለሁ ። የቁጣህ ውጤት አይሁን እንጅ አንተ በኔ ላይ ይሆን ዘንድ የወደድከዉን ሁሉ ወድጃለሁ። ምንም አድርገኝ ከቶም ግድ የለኝ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
287 viewsMohammed Seid, 15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 22:04:55 ዛሬ ዙል-ሒጃ 29 ቀን ነው፡፡ ተነገ ወድያ ኢንሻአላህ አዲሱ ዓመተ ሂጅራ ይጀምራል፡፡ ሙሐረም 1444፡፡
ሙሐረም የተከበረው የአላህ ወር በመባል ይታወቃል፡፡ በዉስጡም ታላቁን ቀን የድል ቀን ዓሹራን ይዟል፡፡ ከረመዷን ቀጥሎ ትልቁ ፆምም የሙሐረም ወር ፆም ነው፡፡
የአላህ መሻት ሆነና ኢስላማዊው አቆጣጠር ሂጅራን መሠረት አደረገ፡፡ ሃይማኖትን ከግፈኞች ለማዳን ከመካ ወደ መዲና የተደረገ ስደት ነው፡፡ ሂጅራ በኢስላም ሃይማኖት ዉስጥ ትልቁን ቦታ ይይዛል፡፡ በሂጅራ ምክንያት ኢስላም መጠጊያ አገኘ፣ አበበ፣ አደገ፡፡

አላህ ሆይ የሂጅራው ባለቤት በሆኑት ታላቁ ነቢይ ሙሐመድ እዝነትህን አዉርድ፡፡ እርሣቸው የተላኩበትን መልዕክት በርግጥ ለዓለማት አደረሱ፣ መከሩ፣ አስተማሩ፣ አመላከቱ፡፡

አላህ ሆይ ወሩንና ዓመቱን ሁሉ መልካም አድርግልን፡፡ በረከትህንና ችሮታህንም ለግሰን፡፡
አላህ ሆይ ሙስሊም አድርገህ አኑረን፣ በእስልምና ላይም ግደለን፡፡

http://t.me/MuhammedSeidABX
381 viewsMohammed Seid, 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 20:13:13 ሙስሊሞቹ በየጎሳዎቻቸው ውስጥ ተሰግስገው በከዕባ) ዙሪያ ተቀምጠዋል። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተቀምጠው እያለ አቡበክር (ረ.ዐ) ንግግር ሊያደርጉ ተነሱ። ንግግራቸውን እንደጀመሩ ቁረይሾቹ በአቡበክር (ረ.ዐ) እና በሙስሊሞቹ ላይ ተነሱባቸው። በተለይ አቡበክርን (ረ.ዐ) ክፉኛ ተረባረቡባቸው። ዑትባህ ኢብን ረቢዐህ ሥሩ ድርብርብና ጠንካራ በሆነ ጫማው ክፉኛ ፊታቸውን ደበደበው። ሆዳቸውንም ረገጣቸው። ፊታቸውና አፍንጫቸው እስከማይለይ ድረስ በጣም ተጎዱ።
በኑ ተይም የሚባሉት የአቡበክር ጎሳ አባላት አቡበክርን ከወደቁበት አነሷቸው። ወደቤታቸው ሲወስዷቸው እንደሞቱ ቆጥረዋቸው ነበር።
አባታቸው አቡ ቁሓፈህ እና የተወሰኑ የበኑ ተይም ሰዎች የአቡበክርን (ረ.ዐ) መንቃት ሲጠባበቁ ውለው በመጨረሻ አመሻሽ ላይ ነቁ። የመጀመርያ ጥያቄያቸው “የአላህ መልዕክተኛን ምን አግኝቷቸው ይሆን?” የሚል ነበር፡፡
በዚህ ጊዜ ሰዎቻቸው ትችትና ወቀሳ ሰነዘሩባቸው። ከዚያ ይልቅ እናታቸው ኡሙል ኸይር የሚቀምሱት ነገር እንዲሰጧቸው አሳሰቧቸው። ኡሙል ኸይር እንደተባሉት ምግብ ይቀምሱ ዘንድ ልጃቸውን ጠየቋቸው። እርሳቸው ግን “የአላህ መልዕክተኛ ምን ገጥሟቸው ይሆን?” በማለት ይወተውቱ ነበር። “በአላህ ይሁንብኝ ስለጓደኛህ የማውቀው ነገር የለም” አሉ ኡሙል ኸይር።
አቡበክር (ረ.ዐ) በዚህ ጊዜ “ወደ ኡሙ ጀሚል ቢንት አል-ኸጣብ ሂጂና ስለርሳቸው ሁኔታ ጠይቂያት” አሉ እናታቸውን።
….
“እርሳቸው በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ” አለች።
“የት ነው ያሉት?” አሉ አቡበክር (ረ.ዐ)።
“በኢብን አል-አርቀም ቤት ናቸው።”
አቡበክር (ረ.ዐ) ይህን ሲሰሙ “የአላህን መልዕክተኛ ሳላይ ምግብም ሆነ የሚጠጣ ነገር አልቀምስም” በማለት ማሉ።
ጊዜው እስኪመሻሽና በጎዳናዎች ላይ ሰዎች እንደማያገኟቸው እስኪያረጋግጡ ከቆዩ በኋላ አቡበክር (ረ.ዐ) በሁለቱ ሴቶች ተደግፈው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደሚገኙበት ሥፍራ አመሩ።
እዚያ ሲደርሱ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከመቀመጫቸው ተነስተው ሲስሟቸው ሌሎች ሶሓቦችም እንዲሁ ሳሟቸው። ከዚያም በደረሰባቸው ሁኔታ ማዘናቸውን ገለጹላቸው።
አቡበክር (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፦ “አባትና እናቴ መስዋዕት ይሁኑልዎ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ያ ተንኮለኛ ፊቴን ክፉኛ የመታኝ ከመሆኑ በስተቀር የደረሰብኝ ችግር የለም። እናቴ ለልጇ በጣም መልካም ነች። እርስዎ ደግሞ የተባረኩ ነዎት። ወደ አላህ ይጥሯት በርስዎ ምክንያት ከእሳት ነጻ ያደርጋት ዘንድም እርሱን ይለምኑላት።”
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ዱዓ ካደረጉ በኋላ ወደ ኢስላም ሲጠሯቸው ኡሙል ኸይር ሰለሙ።

ምንጭ ፡- “አቡበክር አስ-ሲዲቅ” መጽሐፍ
በዶ/ር ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ አስ-ሶላቢ
አሕመድ ሑሴን አቡ ቢላል እንደተረጎመው


 
https://t.me/NejashiPP
291 viewsMohammed Seid, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 17:51:15 ስለ ዱንያ ከተባሉት
****
‹ይህች ዱንያ አገር የሌለው ሰው አገር፤ ገንዘብ የሌለው ሰው ገንዘብ ናት፡፡ እሷን የሚሰበስባትም ዐቅል የሌለው ነው፡፡›   (ዐብዱላህ ኢብኑ ሙስዑድ)
 
‹ዱንያ (የቅርቢቱ ዓለም) ዱንያ የተባለችው በርግጥም ቅርብ ስለሆነች ነው፡፡ ማል (ገንዘብ) ማል (ዘንባይ) የተባለው ባለቤቱን ወደራሱ እንዲያዘነብል ስለሚያደርግ ነው፡፡ (ሱፍያን አስ-ሠውሪይ)

‹ዱንያ ለብልሆች መስሪያ አገር ናት፡፡ መሃይማን ደግሞ በሷ ላይ ተዘናግተዋል፡፡ ከሷ እስኪለቁ ድረስ ስለሷ ምንም አላወቁም፡፡ ወደኋላ ለመመለስ ፈልገው ቢጠይቁም መመለስ አልቻሉም፡፡›  (ወህብ ኢብኑ ሙነበህ)

‹አራት ነገሮች የዕድለ ቢስነት ምልክቶች ናቸው፡፡ የቀልብ መድረቅ፣ የዐይን እንባ ማጣት፣ ረጅም ምኞት እና በዱንያ ላይ ለመቆየት መስገብገብ፡፡› (ሐሰን አል-በስሪ)

‹ለዱንያ ባለህ ሀሳብና ጭንቀት ልክ ለአኺራ ያለህ ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል፡፡ ለአኺራ ባለህ ጭንቀት ልክ ለዱንያ ያለህ ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል፡፡ ለዱንያ በተደሰትክ ልክ የአኺራ ጥፍጥና ከልብህ ውስጥ ይወጣል፡፡ (ማሊክ ኢብኑ ዲናር)

‹በዱንያ ላይ አንድ የሚያስደስትህ ነገር አይኖርም በሌላ በኩል የሚያስከፋህ ነገር የተጣበቀበት ቢሆን እንጂ፡፡ (ሰለመህ ኢብኑ ዲናር)
‹የዒባዳን ጥፍጥና ማግኘትና የጥፍጥናው ጣሪያ መድረስ ከፈለግክ ባንተና በዱንያ ስሜቶች መካከል ከብረት የሆነ ግድግዳ አብጅ፡፡› (ዐብዱላህ አር-ራዚ)
 

‹በሀብቱ ላይ በሚስገበገብ ሰው አትቅኑ፡፡ ሲሳዩ በሰፋለትምና ገንዘቡ በበዛለትም ሰው እንዲህ አትቅኑ፡፡ ሀብትም ሆነ ንብረት ደስታ አይሆንም፡፡  የዚህ ዓይነቱን ሰው ደስ በማያሠኝ መልኩ እዩት፡፡  ዛሬ በባከነበት ነገር ምክንያት ነገ መጨረሻው ሊሆን ስለሚችል ነገር አስቡና በአዘኔታ ዐይን ተመልከቱት፡፡ መስገብገብ ሁለት አይነት አለው፡፡ መጥፎ እና ጠቃሚ፡፡ ጠቃሚ የሚባለው በአላህ ትዕዛዛት ላይ መስገብገብ (መጓጓት) ነው፡፡ መጥፎው በዱንያ ጉዳዮች ላይ ዕረፍት ሳያጡ መሰብሰብ፣ በውጥረት መኖር፣ ራስን መቅጣትና በሰበሰቡትም አለመርካት ነው፡፡› (ዐብዱልዋሒድ ኢብኑ ዘይድ)

‹አንድ ሰው ዱንያው ስትጨምርና አኺራው ስትቀንስ እያየ ይህን ሁኔታውን ወዶ የሚኖር መሆኑን ካየህ የዚህ ዓይነቱ ሰው የተታለለና ሳያውቅም በራሱ የሚጫወት መሆኑን እወቅ፡፡› (ሰዕድ ኢብኑ መስዑድ)

‹ዱንያችሁን በአኺራችሁ ሽጡ፡፡ ወላሂ ሁለቱንም ታተርፋላችሁ፡፡ አኺራችሁን በዱንያ አትሽጡ ወላሂ ሁለቱንም ትከስራላችሁ፡፡› (ከሢር ኢብኑ ዚያድ)


 
https://t.me/NejashiPP


https://bit.ly/3r4948i
357 viewsMohammed Seid, 14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 21:09:28 ዱንያ ላይ ያለን ሀብት ሁሉ ከሚኖረኝ
ሰብሓነላህ
አልሐምዱ
ላ ኢላሀ ኢልለሏህ
አሏሁ አክበር ማለትን እመርጣለሁ። ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ ሶ.ዐ.ወ።

https://t.me/NejashiPP
89 viewsMohammed Seid, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 21:57:54 በዙርያህ ያሉትን ማስደሰት፣ በዙርያህ ላሉት መኖር፣ ሓጃቸዉን ማውጣት፣ ጉዳያቸዉን መፈፀም፣ ማማከር፣ ማበረታታት፣ ወርዶ መጫወትና ማጫወት፣ ማውጋት፣ በዉስጣቸው ተስፋን መዝራት፣ ማብሰር፣ ደስ እንዲላቸው ማድረግ፣ ለነርሱ ደስታ መደሰት ምንዳ ያለው ዒባዳ ነው፡፡ አላህን እና ረሱሉን ማስደሰት ነው፡፡
“የአንድ ወንድሜን ሓጃ መፈፀም በዚህ መስጂድ ዉስጥ ወር ኢዕቲካፍ ከመቀመጥ እመርጣለሁ፡፡" ይሉ ነበር ሐቢባችን ሶ.ዐ.ወ።

http://t.me/MuhammedSeidABX
122 viewsMohammed Seid, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 21:42:10
281 viewsMohammed Seid, 18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ