Get Mystery Box with random crypto!

አንተ አሁን የምታገኘውን ውጤት አይደለህም አሁን እያገኘህ ያለኸው ምንም ዓይነት ውጤት ያንተ የድ | Motivational Speech & Truth

አንተ አሁን የምታገኘውን ውጤት አይደለህም

አሁን እያገኘህ ያለኸው ምንም ዓይነት ውጤት ያንተ የድንቁ ሰው መገለጫ ሳይሆን፣ የአምና ወይም ያለፉት ቀናት የአሰራርህና የአኗኗርህ ውጤት ነው።

እስከ ዛሬ ድረስ ትኖርበት የነበረው ዘዴ ድንቅ ከሆነ፣ አሁን የምታገኘውም ውጤት ድንቅ ነው የሚሆነው፣ በተቃራኒው እስከ ዛሬ ትሰራበትና ትኖርበት የነበረው ውጤት ተራ ከሆነ ደግሞ አሁን የምታገኘውም ውጤት ተራ ነው የሚሆነው፣ ስለዚህ አሁን የምታገኘው ውጤት ምንም ሆነ ምን፣ የምርጫ መብት እንዳለህና የወደድከውን ነገር ማድረግ እንደምትችል አትርሳ፣ አንተ ልዩና ድንቅ ነህ፣ ከአሁን ጀምሮ ድንቅ ለመሆን በመምረጥ ድንቅ ሥራዎችን በመሥራትና መሥዋዕትነት መክፈል ላሉብህ ጉዳዮች መሥዋዕትነት በመክፈል፣ ከፊትህ ለሚመጡት ቀናት የምትፈልገውን ድንቅ ውጤት ማጨድ ትችላለህ።

መልካም ቀን