Get Mystery Box with random crypto!

በድጋሜ የተላለፈ ማስታወቂያ | M.O.R East Addis Ababa Branch

በድጋሜ የተላለፈ ማስታወቂያ ለምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች በሙሉ

ከፌዴራል ገቢ በተጨማሪ የሥራ ግብር እና የጡረታ ታክሶችን በኦን ላይን መክፈል መጀመራቸውን ስለማሳወቅ

ታክስን በኤሌክትሮኒክስ ለመሰብሰብ በተደረገው የአገልግሎት አሰጣጥ ስምምነት መሰረት ከዚህ በታች በተጠቀሱት የመንግስትና የግል ባንኮች ማለትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ ብርሃን ባንክ፣ ህብረት ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ ኦሮሚያ ባንክ፣ ዘመን ባንክ፣ ቡና ባንክ፣ እናት ባንክ እና ደቡብ ግሎባል ባንክ የአገልግሎት አሰጣጥ ስምምነት ፈርመው መስተንግዶ በመስጠት ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ስለሆነም፡-

1. በፌዴራል የሚሰበሰቡ ታክሶችና ወጪ መጋራትን ጨምሮ ብሄራዊ ባንክ በሚገኘው የኤሌክትሮኒክስ የገቢዎች ሚኒስቴር የቀጥታ ታክስ የሒሳብ ቁጥር

2. የአዲስ አበባ የደመወዝ ገቢ ግብርና የኪራይ ገቢ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚገኘው የኤሌክትሮኒክስ መክፈያ ሂሳብ ቁጥር እንዲሁም


3. የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጄንሲ የጡረታ ክፍያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚገኘው የኤሌክትሮኒክስ መክፈያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር መፈፀም የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለሁሉም ክፍያዎች ትክክለኛውን የባንክ የሒሳብ ቁጥር; በዋናነት የሰነድ ቁጥር በመጠቀም ይህ ማስታወቂያ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ግብራችሁን በባንክ እንድትከፍሉ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ክፍያዎን ከላይ በተገለፁት ባንኮች ብቻ እንዲፈፅሙ እያሳሰብን፤ ከላይ ከተዘረዘሩ ባንኮች ውጪ ክፍያ ብትፈፅሙ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አውቃችሁ ቅ/ጽ/ቤቱም ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡